የሲዳማ ዞን የካቢኔ ሽግሽግ የመተካካት ፖሊስን የተከተለ ነውን?

ጥቻ ወራና (Xiichcha Woraana) ከሲዳማ እንደ ዘገበው፤የቀድሞ የሲዳማ ዞን መንግስት ዋና ኣስተዳዳሪ የነበሩትን ካላ ሚሊዮን ማቲዎስ ከሲዳማ ዞን ለቀው ወደ ክልል ያመሩ ሲሆን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃለፊ ሆነዋል። በካላ ሚሊዮን ማቲዎስ ቦታ ከሃርቤጎና እንደመጡ የምነገርላቸውን የቀድሞው የዞኑ የድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ካላ ኣክልሉ ኣዴላ ተተክተዋል። በካላ ኣክልሉ ቦታ ደግሞ ካላ ደስታ ላታሞ የዞኑ ድርጅት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ሆነው ተሹመዋል።

በተመሳሳይም የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ሀላፊ ሆነው ስሰሩ የቆዩት ካላ በቀለ ታፎ ወደ ሲዳማ ዞን ስቪል ሰርቪስ መምሪያ ተዛውረዋል። በካላ በቀለ ቦታ የቀድሞ የሸቤድኖ ወረዳ ዋና ኣስተዳዳሪ ካላ ታረቀኝ ጋቤራ ተተክተዋል።

የሲዳማ ዞን የካቢኔ ሽግሽግ በተመለከተ ጥቻ ወራና ያሰባሰብናቸው የህዝብ ኣስተያዬት እንደምያመለክተው፤ ሰሞኑን በሲዳማ ዞን ኣስተዳደር የተደረገው የካቢኔ ሽግሽግ የኣገሪቱ መንግስት በመከተል ላይ ያለውን የመተካካትን ፖሊስ ተግባራዊ ያላደረገ ነው። የካቢኔ ሽግሽጉ የዞኑን የመምሪያ ሃለፊዎች ከመምሪያ ወደ መምሪያ የቀያየር እንጂ የመተካካትን ፖሊስ ተግባራዊ በማድረግ ኣዳዲስ መሪዎችን ያመጣ ኣይደለም። እንደነዚሁ ኣስተያየት ሰጪዎች ከሆነ፤ ጉልቻ መቀያየር ወጥ ኣያጣፍጥም እንደምባለው ሀላፊዎችን ከመምሪያ ወደ መምሪያ መቀያየር ብዙም ለውጥ ኣያመጣም ብለዋል።


በተመሳሳይም የካለ ሚሊዮን ማቲዎስ ወደ ክልል ትምህርት ቢሮ መዛወራቸውን በርካታ ኣስተያየት ሰጭዎች የተቃወሙ ሲሆን፤ የካላ ሚሊዮን ኣባት ካላ ማቲዎስ ለሲዳማ ህዝብ መብት መከበር ያደረጉትን መስዋዕትነት ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እና ካላ ሚሊዮን የዞኑ ዋና ኣስተዳደሪ በመሆን በቆዩባቸው ኣመታት በሲዳማ ዞን ውስጥ መልካም ኣስተዳደር ለማስፈን ባደረጉት ጥረት የሲዳማ ዞን ህዝብ የምወዳቸው በመሆኑ የምወዳቸውን ህዝብ በትጋት እና በሃላፊነት ማገልገል እያለባቸው ወደ ክልል መሄዳቸው እንዳዛዘናቸው ኣመልከተዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር