የሲዳማ ቡና ኣምራቾች በዚህ ኣመት የቡና ገበያ የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ የዞኑ መንግስት የተለያዩ የገበያ ኣማራጮችን መፍጠር ይጠበቅበታል

Photo: James Jeffrey/IRIN
የሲዳማ ዞን በኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ ከፍተኛ የቡና ምርት የምመረትባት ዞን ናት። ኣብዛኛው ማለትም ወደ 80 ከመቶ የምሆነው የዞኑ ነዋሪ ኑሮውን የምደግፈው በግብሪና ስራ ላይ ተሰማርተው ሲሆን፤ የቡና ምርት በዞኑ ውስጥ ከዌሴ ምርት ቀጥሎ በግንባር ቀደምትነት በመመረቱ የሚጠቀስ ነው። ሲዳማዎች በስማቸው በምጠራው የቡና ኣይነት ወይም የቡና ምርት ምልክት/ መጠሪያ በኣለም ላይ የሚታወቁ ሲሆን፤ በቡና ምርታቸው የምታወቁት ያህል ከሽያጩ ተጠቃሚ ኣይደሉም። የኣለምን የቡና ገበያ የተመለከቱ መረጃዎች እንደምያሳዩት ከሆነ፤ በቡና ምርት ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ በማጋበስ ላይ የምገኙት የሲዳማ ቡና ኣምራቾች ሳይሆኑ የሲዳማን ቡና ቆልተው እና ፈጭተው የሚቸረችሩ ኩባኒያዎች ናቸው።

እነዚህ ኩባኒያዎች ከሲዳማ ቡና ኣምራቾች በዝቅተኛ ዋጋ የሚገዙትን ቡና በመሸጥ በሚያገኙት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ ኢኮኖሚያቸውን እያፈረጠሙ ሲሆን፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች ግን ከምርታቸው ተጠቃሚ ካለመሆናቸው የተነሳ በሚያጋጥማቸው ኢኮኖሚያዊ ችግር የቀን ተቀን ኑሮ ኣስቸጋሪ እየሆነባቸው ነው።

ከቅርብ ኣመታት ወዲህ በጉዳዩ ዙሪያ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን የወሰደ ሲሆን፤ የቡና ኣምራቾችን በማህበር በማደራጀት በኢትዮጵያ የምርት ገበያ በኩል የቡና ኣምራች ማህበራቱ ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለኣለም ገበያ እንድያቀርቡ መደረጉን እንደኣብነት ማንሳት ይቻላል። ይህ የመንግስት እርምጃ የማህበራቱ ገብ በኣንጻሩ ያሳደገው ብሆንም በቡና ኣምራች ኣርሶ ኣደሩ ገብ ላይ ያመጣው ለውጥ ይህን ያህል ነው።

በኢትዮጵያ፤ ፓናማ እና ኢልሳልቫዶር በብሄራዊ የቡና ማህበራት በኣማካሪነት ያገለገሉት ካላ ዊልያም ቦልት እንደምሉት ከሆነ፦ የሲዳማ ቡና ኣምራቾች ብሎም የኢትዮጵያ ቡና ኣምራቾች ከምያመርቱት ጥራት ካለው የቡና ምርት ኣንጻር ከቡና ሽያጩ የምያገኙት ገብ ዝቅተኛ ነው።

ስለዚህ ከዘንድሮው የቡና ምርት የሲዳማ ቡና ኣምራች ኣርሶ ኣደሮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ኣዲሱ ሉሎ ቡና ገበያ ከማጥለቀለቁ በፊት በኣለም ኣቀፍ ደረጃ ገበያ በማፈላለግ የቡና ኣምራቾች ማህበሩን የመደገፍ ስራ ከዞኑ መንግስት ይጠበቃል።


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር