ከሀዋሳ ዲላ ያለው መንገድ ስራ እስኪጠናቀቅ ነሪዎች ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ)  ከሀዋሳ ዲላ ያለው መንገድ ርዝመቱ 90 ኪሎ ሜትር ይደርሳል ።
ይህ መንገድ ከተማዎቹን አቋርጠው ለሚወጡ የንግድና የማህበራዊ አገልግሎቶች ከፍተኛ ደርሻ አለው።
መንገዱ ረዘም ላለ አመታት ያገለገለና ጠንካራ ጥገናም ያልተደረገለት ነው።
አሁን ላይ መንገዱ ለረጅም ጊዜ ከማገልገሉ ጋር ተያይዞ አገልግሎት መስጠት የማይችለበት ደረጃ ላይ መድረሱን በመንገዱ የሚገለገሉ ሰዎች ይናገራሉ።
የአካባቢው ነዋሪዎች መንገዱን ለዚህ ያደረሰው አልፎ አልፎ  የሚደረግለት  መጠነኛ ጥገና በመቋረጡ  ባጠቃላይ ለአንቅስቃሴ አስቸግሯል ባይ ናቸው።
አንዳንዴ ለመኪኖች የርእስ በእርስ ግጭትም ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።
ከዚህ ባለፈም የመንገዱ ምቹ አለመሆን የተሽከርካሪ እቃዎች ላይ የሚያደርሰው ችግርን የከፋ አድርጎታል።
ባለንብረቶችም ይህም  ያሳሰበ ጉዳይ ሆኖብናል እናም የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጠው ይላሉ።
በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር  አቶ ሳምሶን ወንድሙ  እንደሚሉት ከሀዋሳ በሀገረ ማርያም እስከሞያሌ የሚደርስ መንገድ አለ።
ይህ መንገድ ደግሞ በስድስት ኮንትራክተሮች ተከፋፍሎ የሚሰራ ሲሆን አሁን ቅሬታ የተነሳበት ከሀዋሳ እስከ ዲላ ያለው መንገድም  ከሀዋሳ ሀገረ ማርያም በሚደርሰው የመንገድ ከፍል ግንባታው በያዝነው አመት የተጀመረ ነው ይላሉ።
በርግጥ አሁን ከሀዋሳ እስከዲላ ያለው መንገድ ረዘም ላሉ አመታት የአገልግሎት የሰጠ መሆኑን የሚያስታውሱት አቶ ሳምሶን ይህ ደግሞ መንገዱ አሁን መስጠት የሚገባውን አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጎታል ባይ ናቸው።
በመሆኑም በነዋሪው የሚነሳው ቅሬታ ተገቢ መሆኑ ላይ ይስማማሉ።
አቶ ሳምሶን  ይህ መንገድ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን መኪኖች ከሚያስተናግዱ መንገዶች መካከል መሆኑንም ተናግረው መንገዱን በአስፋልት ደረጃ መስራቱ እንዳለ ሆኖ ሌሎች ጊዜያዊ የመፍትሄ እርምጃዎችም ይከናወናሉ ይላሉ።
 አቶ ሳምሶን አሁን ባለስልጣኑ የሚያከናውነው ስራ ችግሩን በዘላቂነት የሚፈታ ነው በማለት  የአካባቢው ነዋሪዎችና በመንገዱ የሚጠቀሙ አካላት እንደስከዛሬ ችግሩን በመጋራት ለመንገዱ መጠናቀቅ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር