በሲዳማ ለኣያሌ ኣመታት ብቸኛ ኣስፓልት መንገድ ሆኖ የቆየው ሃዋሳ - ዲላ መንገድ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በኮንክሪት ደረጃ መገንባት መጀመሩን ኣፊኒ

Hawassa - Dila

ይህን በርካታ ኣመታት በብቸኛ የኣስፓልት መንገድነቱ በሲዳማ ውስጥ የምታወቀው ከሃዋሳ ዲላ የምወስደው መንገድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን በዚህ ኣመት ከ2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ለማሰራት ግንባታውን የጀመረው የሀዋሳ - ቡሌ ሆራ የ198 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ኣካል ሆኗል።
በጣሊያን ጊዜ እንደተሰራ በኣፌ ታሪክ የምነገርለት ይህ መንገድ ካለው ረዥም እድሜ የተነሳ በከፈተኛ ሁኔታ የተጎዳ ነው። በመሆኑም መንገዱ እንደ ኣዲስ ደረጃውን በጠበቀ የኮንክሪት አስፋልትነት መገንባት ብሎም ከ12 እስከ 22 ሜትር ስፋት ይኖረዋል ማድረጉ፤ ቡናን እና ሌሎች የሲዳማ ምርቶችን ወደ ማዕከላዊ ገበያ በፍጥነት እና በጥራት ለማቅረብ ያስችላል። ይህም በሲዳማ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ኣዎንታዊ ተጽዕኖ ቀላል ኣይደለም።
ከዚህም ባሻገር መንገዱ የምያቋርጣቸው ከሲዳማ መዲና ሃዋሳ ጀምሮ እስከ ዲላ ከተማ ያሉ እንዴ፦ ሞኖፖል፤ቱላ፤ኣቤላ ሊዳ፤ ሞሮቾ፤ ማስንቃላ፤ ኣፖስቶ፤ጩኮ እና ሌሎች የሲዳማ ከተሞች  እስከ 22 ሜትር የምሰፋው መንገድ ገጽታቸው እንደምቀይር እና ለስራ እና ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ እንደምያደርጋቸው ይጠበቃል። ይህም በእነዚህ ከተሞች የምኖሩ ሰዎች በቀላሉ ሃዋሳ እና ዲላን በመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች መስራት ያስችላቸዋል።
Tolla Gamaxo Road Sidama

እንደ ፋና ብሮድካስቲን ኮፖሬት ድረ ገጽ ዘገባ ከሆነ፦ መንገዱ ኢትዮጵያን ከኬንያ ከማስተሳሰሩም በላይ በሲዳማ እና ገዴኦ የሚገኘውን ምርት በቀላሉ ለገበያ ለማቅረብ ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እንደገለጹት ፥ የመንገዱ ግንባታ የተጀመረው በኢትዮጵያ መንግስት እና በአፍሪካ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡
መንገዱ ከሀዋሳ - ጭኮ 66 ኪሎ ሜትር ከጭኮ - ይርጋ ጨፌ 60 ኪሎ ሜትር እና ከይርጋ ጨፌ ቡሌ ሆራ 72 ኪሎ ሜትር ሲሆን ፥ በ3 ዓለም አቀፍ ኮንትራክተሮች የሚገነባ ነው ።

በመንገዱ አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የካሳ ክፍያ ተፈጽሞ የግንባታው ሂደት መጀመሩን ያወሱት አቶ ሳምሶን ፥ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ተናግረዋል ።

    

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር