ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ኣንድ ተጫዋች ለብሄራዊ ቡድን ኣስመረጠ

የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት አጋማሽ ይጀመራል
የዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ሻምፒዮና ቅዳሜ ጥቅምት 16 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይጀመራል፡፡
ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ባወጣው ፕሮግራም መሠረት የመክፈቻውን ጨዋታ በ9 ሰዓት የሚያደርጉት ኢትዮጵያ መድንና አርባ ምንጭ ከነማ ሲሆኑ፣ በ11 ሰዓት ቀጣዩ ተጋጣሚዎች መከላከያና ሲዳማ ቡና ይሆናሉ፡፡ በክልል ከተሞች ጨዋታዎቹ ጥቅምት 17 እንደሚጀመሩ ታውቋል፡፡
************* 
የቅዱስ ጊዮርጊስ የዛሬ ጨዋታ መግቢያ ዋጋ ወጣ 
ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ክለቡ ዛሬ መስከረም 12 ቀን በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቱኒዝያው ኤትዋል ዱ ሳህል ጋር ላለበት ግጥሚያ የመግቢያ ቲኬቶች ዋጋ አውጥቷል፡፡
ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በላከው መግለጫ መሠረት፣ ክብር ትሪቡን ብር 300.00፣ ጥላ ፎቅ ግራና ቀኝ ብር 150.00፣ ከማን አንሼ ብር 50፣ የተቀሩት መቀመጫዎች በሙሉ ለፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች በሚከፈለው ዋጋ መሠረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
******* 
ፌዴሬሽኑ ለወሳኙ ጨዋታ 28 ተጫዋቾች መረጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጪው ሰኔ ብራዚል በምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ ተካፋይ ለመሆን ከናይጀርያ አቻው ጋር ላለበት ወሳኝ ግጥሚያ 28 ተጫዋቾችን መምረጡን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አስታወቀ፡፡
ከተመረጡት ተጫዋቾች 10ሩ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ 4ቱ ከደደቢት ሲሆኑ፣ ሦስት ሦስት ያስመረጡት ደግሞ ኢትዮጵያ ቡናና የጎንደሩ ዳሽን ቢራ ናቸው፡፡ አርባ ምንጭ ሁለት ሲያስመርጥ፣ ሲዳማ ቡናና መከላከያ አንድ አንድ አስመርጠዋል፡፡ 
ቅዱስ ጊዮርጊስ፡- ሳምሶን አሰፋ፣ ደጉ ደበበ፣ ቢያድግልኝ ኤሊያስ፣ ሳላዲን በርጌቾ፣ አበባው ቡጣቆ፣ ምንያህል ተሾመ፣ በኃይሉ አሰፋ፣ ምንተስኖት አዳነ፣ አዳነ ግርማ፣ ዑመድ ኡክሪ፤ ደደቢት፡- ሲሳይ ባንጫ፣ ብርሃኑ ቦጋለ፣ ሥዩም ተስፋዬ፣ ዳዊት ፈቃዱ፤ ኢትዮጵያ ቡና፡- ጀማል ጣሰው፣ ቶክ ጀምስ፣ ፋሲካ አስፋው፤ ዳሽን ቢራ፡- ደረጀ ዓለሙ፣ ዓይናለም ኃይሉ፣ አሥራት መገርሳ፤ አርባ ምንጭ፡- ሙሉዓለም መስፍን፣ ገብረ ሚካኤል ያዕቆብ፤መከላከያ፡- መድኃኔ ታደሰ፤ ሲዳማ ቡና፡- ሞገስ ታደሰ፤ ከቤልጂየም፡- ሳላዲን ሰይድ፤ ከደቡብ አፍሪካ፡- ጌታነህ ከበደ፤ ከሊቢያ፡- ሺመልስ በቀለ፤ ከሱዳን፡- አዲስ ሕንፃ፡፡
 ምንጭ፦ሪፖርተር ጋዜጣ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር