በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ቆንስል ጄኔራሎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ ነሐሴ 27/2005 በመላው አለም የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ቆንስል ጄኔራሎችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አዲስ አበባ ውስጥ እየመከሩ ነው። ለአንድ ሳምንት የሚቆየውን የምክከር መድረክ የከፈቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሐኖም አንዳሉት በዲፕሎማሲ ሰራዊት ግንባታ፣በቢዝነስ ዲፕሎማሲ፣በንግድ፣በቴክኖሎጂ ሽግግር፣በኢንቨስመንት፣ብድርና እርዳታ በማፈላለግ፣በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን በማንቀሳቀስ፣ በባህልና ቱሪዝም ረገድ አምባሳደሮቹ ያከናወኗቸውን ተግባራት በተመለከተ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በስፋት ይገመግማሉ። ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምና ሰላም እኳያ ከጎረቤት አገሮች ጋር ያለው ግንኙነት በተለይም ከሁለቱ ሱዳኖች ከግብጽና ከሶማሊያ ጋር በተያያዘ ጥልቅ ውይይት ይካሄዳል ብለዋል። በስራ አፈጻጸማቸው መልካም ተመክሮ ያላቸው ኤምባሲዎች ልምዳቸውን ለሌሎች የሚያካፍሉበት ልዩ መድረክም ተመቻችቷል። ኢዜአ ያነጋገራቸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ቋሚ መልእክተኛ ዶክተር ተቀዳ አለሙ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ የአገሪቱን ጥቅም ከማራመድ ባሻገር የአካባቢውን አገራት እና የአፍሪካን ጥቅም በሚገባ የምታስከብር አገር ስለመሆኗ ጠንካራ አመኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ሊመቀንበር በመሆኗ የአህጉሪቱን ጥቅም ለማስከበር በመርህ ላይ ተመስርታ ጠንካራ እንቅስቃሴ እያደረገች በመሆኗ በመንግስታቱ ድርጅትና በአፍሪካ አገራት ዘንድ ያላት ተቀባይነት እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ጥቅምና ወዳጅነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ለመመሰረት የበርካታ አገራት ፍላጎት መሆኑንም ጠቁመዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አምባሳደሮቹ በቡድንና በተናጠል የሚያደርጉትን ውይይት ካጠናቀቁ በኋላ የፊታችን አርብ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የኢንዱስትሪ ተቋማትን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ተናግረዋል።
http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=11493

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር