ጎል ዶት ኮም ትናንት ይዞት በወጣው ዘገባው እንዳመለከተው በርካታ ናይጄሪያውያን በደርሶ መለሱ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲደርሳቸው እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር

New

ዋልያዎቹ ለብራዚሉ የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ናይጄሪያን ይገጥማሉ
አዲስ አበባ መስከረም 06/2005 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለ14ኛው የብራዚል የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታ ከናይጄሪያ ጋር ተደለደለ። ካይሮ በሚገኘው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ጽህፈት ቤት ዛሬ ይፋ በተደረገው ድልድል ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን በመጪው ጥቅምት ወር አዲስ አበባ ውስጥ ከናይጄሪያ ጋር የምታደርግ ሲሆን የመለሱን ደግሞ በኅዳር ወር ከሜዳዋ ውጭ ሌጎስ ውስጥ ታካሂዳለች። የመጀመርያ ዙር ጨዋታው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጥቅምት 11 እስከ 15 ባለው ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን የመልስ ጨዋታው ደግሞ ከኅዳር 15 እስከ 19 ቀን 2013 እንደሚካሄድ ታውቋል። ዛሬ በወጣው የድልድል ዕጣ ኮቲዲቯር ከሴኔጋል፣ ካሜሩን ከቱኒዝያ፣ ጋና ከግብጽ እንዲሁም ቡርኪና ፋሶ ከአልጄሪያ ጋር አገናኝቷል። ጎል ዶት ኮም ትናንት ይዞት በወጣው ዘገባው እንዳመለከተው በርካታ ናይጄሪያውያን በደርሶ መለሱ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲደርሳቸው እንደሚፈልጉ ገልጸው ነበር። እናም ዛሬ የናይጄሪያውያን ምኞት ሰምሮ ሱፐር ኤግሎቹ ዋልያዎቹን ለመግጠም ተደልድለዋል። ያም ሆኖ ስም ያላቸውን ቡድኖች መጣል የለመዱት ዋልያዎቹ ፈታኝ ተጋጣሚ እንደሚሆኑ በርካታ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን በዘገባቸው አመልክተዋል። ናይጄሪያውን በድልድሉ ደስተኞች መሆናቸውን ቢገልጹም ከደቡብ አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ ዋልያዎቹ ከፍተኛ መሻሻል ማሳየታቸውን እንደስጋት ተመልክተውታል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር