ኣብዛኛው ተማሪ ኣንደኛ ምርጫ የሆነውን ትምህርት ኣይነት እና ዩኒቨርሲቲ በማያገኝበት ሁኔታ፤ ዩኒቨርሲቲን እና የትምህርት ክፍል መቀያየርን መከልከል ምን ይሉታ?


ዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት ክፍል መቀያየር አይቻልም - ትምህርት ሚኒስቴር


አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች አድራሻቸውን ጭምር በመጠቀም የዩኒቨርሲቲ እንቀያየር ማስታወቂያ ሲለጥፉ ይስተዋላል።
ይህ ጉዳይ በተለይም በአዲስ አበባ አራት ኪሎ አካባቢ በስፋት ይስተዋላል ፤ አዲስ ገቢ ተማሪዎችም ይህን አካባቢ በብዛት ያዘወትሩታል።
ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከተለያዩ ሰዎች በሚያገኙት መረጃ መሰረት ዝውውሩን ለመጠየቅ ይነሳሳሉ።
የተመደቡበት ቦታ ምቹ አይደለም በሚል ፣ ከቤተሰብ መራቅ ባለመፈለግ ፣ የተመደቡበት የትህርት ክፍል ከምርጫቸው ጋር አይጣጣምም የሚሉት ለዝውውሩ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ።
ተማሪዎቹ ከሚለጥፏቸው ማስታወቂያዎች በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲ የሚቀያየሩ ተማሪዎችን እናገናኛለን የሚሉ እና በአጋጣሚው ለመጠቀም የሚሞክሩ ግለሰቦችም ይስተዋላሉ።
የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ የዩኒቨርሲቲም ሆነ የትምህርት ክፍል ዝውውር አይፈቀድም ይላል።
በሚኒስቴሩ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ሳሙኤል ፥ ተማሪዎቹ ባስመዘገቡት ውጤት እና በሞሉት ምርጫ መሰረት የተመደቡ በመሆኑ ጉዳዩ አይታሰብም ባይ ናቸው።
አያይዘውም አዲሶቹም ሆኑ ነባሮቹ ተቋማት በሚገባ እና በሚሰጡት ትምህርት አግባብ የተደራጁ በመሆናቸው የትም ቢመደቡ ተማሪዎቹ ስጋት እንዳይገባቸውም ነው የተናገሩት።
ከዚህ ባለፈ ግን የሚቀያየሩ ተማሪዎችን እናገናኛለን ከሚሉ ህገ ወጦችም ራሳቸውን ይጠብቁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር