በጤና ተቋማት የሚወልዱ የሲዳማ እናቶች ቁጥር መጨመሩ እየተነገረ ነው

Recién nacido en Aroressa (©F. Schwieker-Miyandazi).
አዋሳ መስከረም 16/2006 በሲዳማ ዞን በአንድ ለአምስት አደረጃጀትና በጤና ልማት ሰራዊት የተቀናጀ ጥረት በተከናወኑ ስራዎች በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የጤና ልማት እቅድ የስራ ሂደት ባለሙያ አቶ አበበ በካዬ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እናቶች በጤና ተቋም እንዲወልዱ በማድረግ የእናቶችና ህፃናትን ሞት ለመቀነስ የሚደረገው ጥረት አበረታታች ነው፡፡ በዞኑ ሁሉም ወረዳ በአንድ አምስት አደረጃጀት፣ በጤና ልማት ሰራዊትና በጤና ኤክስቴንሽን አማካኝነት ህብረተሰቡን በማስተባበር የተከናወኑ ስራዎች በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ40 ሺህ በላይ እናቶች በጤና ተቋማት የወሊድ አገልግሎት ተጠቀሚ መሆን በመቻላቸው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ10 ሺህ ብልጫ አለው ብለዋል፡፡ መምሪያው የወሊድ አገልግሎቱን በሁሉም ጤና ተቋማት በነፃ እንዲሰጥ በማድረጉ ወደ ጤና ተቋም ሄደው የቅድመ ወሊድ፣ የወሊድና የድህረ ወሊድ እንዲያገኙ ድጋፍ መደረጉ ለቁጥሩ መጨመር አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡ የወሊድ አገልግሎት ካገኙት እናቶች መካከል 11 ሺህ በአዋላጅነት በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ሲሆን ቀሪዎቹ በጤና ኤክስቴንሽን አማካኝነት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በየቀበሌው የተመደቡ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ከአከባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር ሁሉም እናቶች ከጤና ተቋም ውጭ እንዳይወሊዱ የሚያደርጉት ሁሉ አቀፍ ጥረት ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡ በዞኑ በጤና ተቋም የሚወልዱ እናቶች ቁጥር ባለፉት ሶስት ዓመታት በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ መጥቷል፡፡ የቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎቱን በማጠናከር ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰት የጤና ችግሮችና የህፃናት ሞትን ለመቀነስ መምሪያው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በተያዘው የበጀት ዓመት " አንድም እናት በቤት ውስጥ የማትወልድበትን ቀበሌ እንፈጥር" በሚል መርህ ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች በጤና ተቋም እንድወልዱ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=12188&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር