የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አይተገበሩም ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 24 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንሰ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፋይናንሰ ግልጸኝነትን ለማስፈን የሚሰራውን ሰራ ለማሳካት በመስኩ የወጡ ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ አንዲተገበሩ አሳሰበ።

በፋይናንስ ግልጸኝነት ዙሪያ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አዳራሽ ዛሬ ተካሂዷል።
በምክክር መድረኩ ላይ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወይዘሮ ገነት ታደስ እንዳሉት ፥ ኢትዮጵያ ከፋይናንስ አሰራሯ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ያደረገቻቸው ህጎችና መመሪያዎች አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መሆናቸውን እና በዚህ ረገድ እየተከናወነ ያለው ስራ በየጊዜው ለውጥ እየታየበት መሆኑን አንስተዋል።
ይሁንና ህጎች በአግባቡ አለመተግበርም እየታዩ ያሉ ችግሮች በመሆናቸው የወጡትን ህጎችና መመሪያዎች በአግባቡ በመተግበር ረገድ የሚመለከታቸው ሁሉ ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ነው ያሳሰቡት።
በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የፋይናንስ ግልጽኝነትና ተጠያቂነት ቡድን መሪ አቶ አለባቸው በላይነህ በበኩላቸው ፥ የፋይናነስ ግልጸኝነትን ለማስፈን በሚሰራው ስራ ሰፊ የግንዛቤ ማስፊያ ስራዎች እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ተቋማት ችግሮቹ ሳይፈጠሩ በፊት ማከናወን የሚገባቸውን ሁሉ በአግባቡ መወጣት አለባቸው ነው ያሉት ህብረተሰቡም ከሚበጀቱ ፋይናንሶች ጋር በተያያዘ በየጊዜው ግንዛቤው እያደገ መምጣቱን በማንሳት ።
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ፣ የፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም የተለያዩ ክልሎች የሚመለከታቸው አካላት የስራ ሀላፊዎች  በምክክር መድረኩ ላይ ተገኝተዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር