በሃዋሳ ከተማ ከ593 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ስራዎች ይከናወናሉ

ሀዋሳ ጳጉሜ 05/2005 በሃዋሳ ከተማ በተያዘው በጀት አመት ከ593 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ የልማት ስራዎች እንደሚካሄዱ የከተማው አስተዳዳር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ አስታወቀ ። በበጀት አመቱ በከተማዋ የሚካሄዱት የልማት ስራዎች የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንዲሁም የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች ታሳቢ ያደረጉ ናቸው። በከተማዉ ከሚከናወኑት የልማት ስራዎች መካከል የተለያዩ ደረጃ ያላቸው የመኪና መንገዶች ግንባታ ፣በመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፣ በትምህርት ተዳራሽነትና ጥራት ፣ በጤና፣ የተፈጥሮና የአካባቢ ጥበቃና በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮሩ ናቸዉ ። በተለይ በመንገድ ልማት ዘርፍ ስድሳ ኪሎ ሜትር የኮብል ስቶን፣ 30 ኪሎ ሜትር ደረጃ የማሳደግና አዲስ የአስፋልት ፣ 120 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገዶች ጥገና እንደሚካሄድ የመምሪያው ምክትል ኃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አመልክተዋል ። በትምህርት ዘርፎችም ሶሰት የመጀመሪያ ደረጃና ሁለት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ፣50 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች የሚገኑ ሲሆን በጤናዉ ዘርፍም የአንድ ጤና ጣቢያ ግንባታን ማጠናቀቅና የአንድ ሆስፒታል ግንባታ እንደሚጀመር አመልክተዋል ። የከተማውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የማሻሻል ፣የተቀናጀ የቤቶች ልማት የማካሄድ እንዲሁም የከተማው ፅዳትና ውበት የማስጠበቅና የመናፈሻ ስፍራዎችን የማደራጀት ስራዎች እንደሚገኙበት ገልጠዋል ። ለስራዎቹ ማስፈፀሚያ የሚያስፈልገው ከ593 ሚሊዮን ብር በላይ በላይ በጀት ከከተማው አስተዳደርና ከመንግሰት ግምጃ ቤትና ከሌሎችም የገንዘብ ምንጮች የተመደበ መሆኑም ተመልክቷል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11723&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር