ሪፖርተር ጋዜጣ 3 ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች ከሃላፊነታቸው ተነሱ በማለት ያወጣው ዘገባ መሰረተ ቢስ ነው-የደቡብ ክልል

ሪፖርተር ጋዜጣ በነሃሴ 29/2005 እትሙ “የደቡብ ክልል 3 ምክትል ርእሰ መስተዳድሮችከሃላፊነታቸው ተነሱ” በማለት ያወጣው ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡
መግለጫው የክልሉ መንግስት የልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራትን በአንድ መንፈስ እያካሄደ በሚገኝበት ወቅት ጋዜጣው ይህን መሰል መሰረተ ቢስ ዘገባ ማሰራጨቱ  አሳዛኝ ድርጊት ነው ብሏል፡፡
የሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ የሀገሪቱን ህጎች የሚፃረር በመሆኑ የክልሉ መንግስት ተግባሩን የፈፀሙት አካላት ህጉን በሚያዘው መሰረት ተከታትሎ  ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑንም ገልጿል፡፡
ምንጭ፡- የደቡብ ክልል የመንግስት ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር