ኮሚሽኑ የተሿሚዎችን፣የተመራጮችንና የመንግሥት ሠራተኞች የሀብት ምዝገባ የሚይዝበትን ስምምነት ተፈራረ

አዲስ አበባ ነሐሴ 14/2005 የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተሿሚዎችን፣የተመራጮችንና በሕግ ግዴታ የተጣለባቸውን የመንግሥት ሠራተኞች የሀብት ምዝገባ በመረጃ ቋት የሚይዝበትን ስምምነት ከአንድ ኩባንያ ጋር ዛሬ ተፈራረመ። ኮሚሽኑ ሲ ኤስ ኤም ሳይበርቴክ ሶፍት ዌር ኤንድ መልቲ ሚዲያ ከተባለው የሕንድ የግል አማካሪ ተቋም ጋር የተደረገው ስምምነት ለሀብት ምዝገባው የሚያስፈልገውን ሶፍት ዌር ለማሰራት ያስችላል። ለፍትህ ሥርዓት ማሻሻያ ሥርዓት ከተመደበው 198ሺህ 530 ዶላር ድጋፍ የሚሰራው ሶፍት ዌር በፌዴራል ደረጃ የተመዘገቡ 60ሺህ አስመዝጋቢዎችን ሀብት ምዝገባ ውጤት ለሕዝብ ክፍት እንደሚያደርግም ኮሚሽኑ አመልክቷል። የሶፍት ዌር ሥራው ሲጠናቀቅ በሀብት ምዝገባው ዓዋጅ መሠረት ውጤቱን ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ከማገዙም በላይ፤በቀጣይ ሀብታቸውን የሚያስመዝግቡ ግለሰቦች ባሉበት ሆነው የመመዝገቢያውን ቅጽ በማውጣት መመዝገብ ይችላሉ። ኮሚሽኑ ከክልሎች የሥነ ምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች ጋር ያለውን የመረጃ ልውውጥ እንደሚያቀላጥፈው መግለጹን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገባ አስታውቋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11046&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር