በሲዳማ ዞን ከበልግ እርሻ ከስድስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት ተሰበሰበ

አዋሳ ነሐሴ 3/2005 በሲዳማ ዞን በምርት ዘመኑ በበልግ ከ100 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር በመሸፈን ከስድስት ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ። በመምሪያው የግብርና ልማት እቅድና ዝግጅት የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በግብርናው ዘርፍ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማረጋገጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የምርጥ አርሶ አደሮችን ተሞክሮ ከማስፋት ባሻገር የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ በልግ አምራች በሆኑ ወረዳዎች 102 ሺህ 785 ሄክታር መሬት በአትክልትና ፍራፍሬ በስራስርና በቆሎ በመሸፈን ከስድስት ሚሊዮን የሚበልጥ ምርት በመሰብሰብ ከ300 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ባለፈው ዓመት በልግ ከ80 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት በዘር ተሸፍኖ ከአራት ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል የሚበልጥ ምርት መሰብሰቡን ገልጸው ያለፈውን አመት መልካም ተሞክሮ በመቀመር ዘንድሮ ከፍተኛ ምርት መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=10683&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር