ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ህዝብ በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ የተከበረውን የሲዳማ ኣዲስ ኣመት የፊቼን በኣል በተመለከተ ከክልሉ ሚዲያ ውጭ ያሉት ኢቲቪን ጨምሮ የኣገሪቱ ትላልቅ የሚዲያ ኣውታሮች ሽፋን ኣለመስጠታቸው ኣነጋጋሪ ሆኗል

የወራንቻ ኔዎርክ የኣገሪቱን ትላልቅ ጋዜጦችን እና የሚዲያ ኣውታሮች ዌይብ ሳይቶች ላይ ባደረገው ቅኝት መረዳት እንደተቻለው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፤ ሬዲዮ ፋና፤ ዋልታ፤ እና የኢትዮጵያ ዜና ኣገልግሎት የፊቼ በኣልን በተመለከተ በእለቱ ምንም ዘገባ ኣለማቅረባቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ኣካል የሆነው ኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ግን የጫንባላላን ኣከባበር በተመለከተ በፎቶ የተደገፈ ዜና እለቱ ይዞ ወጥቷል።

ለሲዳማ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የክልሉ ህዝብ ትልቅ ባህላዊ እሴት የሆነውን የፊቼን በኣል በተመለከተ ስለ በኣሉ ኣከባበር የምገልጹ እና በኣሉን የምያስተዋውቁ ዜናዎችን ብሎም ፕሮግራሞችን እነዚህ ትላልቅ የኣገሪቱ የዜና ኣውታሮች ኣለማቅረባቸው፤ የፊቼን በኣል በዩኔስኮ በኣለም ቅርስነት ለማስመዝገብ የምደረገውን ጥረት የዜና ኣውታሮቹ እየደገፉ ኣለመሆናቸውን ያሳያል ተብሏል።


የፊቼን በኣል በኣለም ቅርስነት ለማስመዝጋብ የሲዳማ ዞን ኣስተዳደር እንድሁም የክልሉ መንግስት ከኢትዮጵያ ባህል እና ቱርዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን የምያደርገውን ጥረት የተሳካ ለማድረግ የኣገሪቱ የሚዲያ ኣውታሮች ባህሉን ለኣለም ህዝብ በማስተዋዎች የበኩላቸውን ልወጡ ይገባል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር