በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት በውጤት ተኮር እቅድና የለውጥ ተግባራት እንዲሁም በመልካም አስተደደር ሥራዎች አተገባበር የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የገጠር ቀበሌያት የእውቅና ሽልማት መስጠቱ ተገለፀ፡፡

በሲዳማ  ዞን ዳራ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት በውጤት ተኮር እቅድና የለውጥ ተግባራት እንዲሁም በመልካም አስተደደር ሥራዎች አተገባበር የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና የገጠር ቀበሌያት የእውቅና ሽልማት መስጠቱ ተገለፀ፡፡
የወረዳው ሲቪል ሰርቪስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ዲንጋማ እንደተናገሩት ተቋማት የመፈፀምና የማሰፈፀም አቅማቸውን በማጎልበት የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በተቀላጠፈ አሰራር በመተግበር የለውጥ ሰራዊት እንዲሆኑ እየተሰራ ይገኛል፡፡
የወረዳው ዋና አስ ተዳዳሪ አቶ ደስታ ደኒሶ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት
በሁሉም ተቋማት የውጤት ተኮር እቅድ ትግበራና የመንግስት ሠራተኞች ምዘና ሥርዓትን ከግብ በማድረስ የተነደፈውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
በከተማም ሆነ በገጠር ቀበሌያት የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በአግባቡ በማከናወን ለህብረተሰቡ ተገቢው አገልግሎት መስጠት እንዳለበት የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው ወደ ኃላ የቀሩትም በቀጣይ እንዲበረታቱ ጠይቀዋል፡፡
በበጀት አመቱም በለውጥና የመልካም አስተዳደር ሥራው የወረዳው ግብር፣ ህብረት ስራ ንግድና ኢንዱስትሪና ትምህርት ጽህፈት ቤቶች እንዲሁም ከገጠር 3 ቀበሌያት ከ1 እስከ 3 በመውጣት የዓይነትና የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡ የወረዳው ባህልና ቱሪዝም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንደዘገበው፡፡
ምንጭ፦http://www.smm.gov.et/_Text/16NehTextN605.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር