ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት ኢንዱስተሪዎችን ሊደግፉ ይገባል-ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም

አዲስ አበባ ነሐሴ 11/2005 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ እንደሚገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ አሳሰቡ። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ለ20 ቀናት ሲወስዱ የቆየውን የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ በይፋ ተጠናቋል። የትምህርት ሚኒስቴር 1 ሺህ 700 የሚሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝዳንቶች፣ የዩኒቨርስቲ ፋኩልቲ ዲኖችና የዲፓርትመንት ኃላፊዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር ዛሬ በአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የተጀመረውን አገራዊ ዕድገት ለማፋጠንና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሠልጥኖ የሚወጣው የሰው ኃይል ብቃቱ የተረጋገጠ መሆን ይገባዋል። ለኢንዱስትሪ ልማት መፋጠን እያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ በየአካባቢው ከሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን እንዲቀረፁ በማስቻል ረገድ አስተዋፅኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸውም አመልክተዋል። አገሪቱ ከድህነት ለማውጣት በሚደረገው ጥረት ፈጣንና ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚ የሚያረጋግጥ ቀጣይነት ያለው ሥራ ለመስራት ግብርናው ወሳኝ ሚና መጫወቱን እንደሚቀጥል ጠቁመዋል። የአገሪቱን የግብርና ዘርፍ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን ለማስቻል እየታዩ ያሉትን ጅምር ዕድገቶች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምርና ስርፀት አስደግፈው ሊሰሩ እንደሚገባቸው አቶ ኃይለማሪያም አስገንዝበዋል። በዚህ በኩል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያደርጉትን ጥረት ለመደገፍ መንግሥት በተቻለው አቅም ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። በመላ አገሪቱ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ምሁራንና የመስኩ ባለሙያዎች አገራዊ ዕድገት ለማፋጠንና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል። የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ካባ ኡርጌሳ በበኩላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ለ20 ቀናት በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ሲወስዱ የቆዩትን የመጀመሪያ ዙር የአቅም ግንባታ ሥልጠና ዛሬ በይፋ መጠናቀቁን ገልጸዋል። ሥልጠናው ወሳኝ የሆኑ የአገሪቱን ፖሊሲዎች በመምረጥና ለአመራርነት ሊረዳቸው በሚችሉ ነጥቦች ላይ በማተኮር እንዲሰጥ መደረጉን ጠቅሰው በዚህም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጠንካራ አመራርን ለማፍራት እንዲያስችላቸው አቅም የፈጠረ መሆኑን አስረድተዋል። በዲላ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክና ምርምር ምክትል ፕሬዝዳንት ብርሃኑ በላይነህ ሥልጠናው አመራርን ሊገነባ የሚችል ወሳኝ አቅም እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። በሥልጠናው ያገኘቱን ዓቅም ወደ ተግባር በመለወጥ የትምህርት ሰራዊት በመፍጠር ረገድ አገሪቱ በትምህርት ልማት ዘርፍ በአምስት ዓመቱን ዕቅድ ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት እንደሚጠሩ አስታውቀዋል።
http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=10963

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር