ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ተፋሰስ አካባቢ አንድ ቢሊዮን ችግኝ ይተከላል

አዋሳ ሐምሌ 25/2005 በደቡብ ክልል በበጋ ወቅት በተፋሰስ በለማ ቦታ ላይ እስካሁን ግማሽ ቢሊዮን ሀገር በቀል ችግኝ መተከሉን የክልሉ ተፈጥሮ ሀብት ልማትና አካባቢ ባለስልጣን ገለጸ። የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መሀመድኑር ፋሪስ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ 14 ዞኖችና 4 ልዩ ወረዳ በበጋ ወቅት በህብረተሰብ ተሳትፎ በተከናወነ ተፋሰስ ላይ ችግኞች እየተተከሉ ነው። ለተከላ ከተዘጋጀው አንድ ቢሊዮን ዋንዛ ፣ጥቁር እንጨት ፣ቀረሮ ፣ዝግባና ሌሎች ሀገር በቀል ዝርያ ያላቸው ችግኞች መካከል ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ እስካለፈው ሳምንት ግማሽ ቢሊዮን የሚሆን ችግኝ ተተክሏል ብለዋል። የመለስ ዜናዊን መታሰቢያ አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ 27 ጀምሮ በሚከናወን ዘመቻ ቀሪው ግማሽ ቢሊዮን ችግኝ የሚተከል መሆኑን ገልጸው በክልሉ ከ3 ሺህ በላይ ቀበሌዎች ለመታሰቢያ የሚሆን ፓርክ እንደሚቋቋም ተናግረዋል። በዘመቻው ከ3 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችና በጎ ፈቃደኞች የሚሳተፉ መሆኑን የጠቆሙት አቶ መሀመድ ኑር በክልሉ በለፉት ሁለት ዓመታት በዘመቻ ከተተከሉት ችግኞች መካከል ከ70 በመቶ የሚበልጠው መጽደቁን አስታውቀዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=10363&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር