በሲዳማ ዞን ከ424 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የተለያዩ በሽታዎች መከላከያ ክትባት ተሰጠ ተባለ

ሃዋሳ ነሐሴ 15/2005 በሲዳማ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት አመት ከ424 ሺህ ከሚበልጡ ህፃናት የተለያዩ በሽታዎች መከላከያ ክትባት መሰጠቱን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ ። በመምሪያዉ የጤና ልማት እቅድ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አበበ በካዬ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጡት መንግሰት ለህፃናትና እናቶች ጤና መጠበቅ በሰጠው ትኩረት በሽታን አስቀድሞ የመከላከሉ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። በዞኑ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች እድሜያቸው ከአንድ አመት በታች ለሆናቸዉ 424 ሺህ 126 ህፃናት የፖሊዮ ፣ የቲቢ፣ የኩፍኝና የሳንባ ምች በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን አስታዉቀዋል ። በዞኑ በመደበኛ የክትባት አገልግሎት በበጀት አመቱ 105 ሺህ 910 ህፃናት መከተባቸውንም አስረድተዋል። በተጨማሪ 15 ሺህ ለሚሆኑ ከፍተኛ ምግብ አጥረት ችግር ላለባቸው ነፍስጡር እናቶችና ህፃናት የተለያዩ አልሚ ምግቦች እንደተሰጣቸውና ከ 80 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የቫይታሚን ኤ እደላ መደረጉንም አስረድተዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=11072&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር