የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ415 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚያካሄደው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ህንጻ ግንባታ በመፋጠን ላይ ነዉ

ሃዋሳ ነሐሴ 8/2005 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመንግስት በተመደበለት 415 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚያካሄደው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፕሮጀክት ህንጻ ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን ገለጸ፡፡ ዩኒቨርሰቲው በ2006 የሚያስጀምራቸው ግንባታዎች ጨምሮ ከ2 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶች እንደሚያካሂድም ተመልክቷል፡፡ በዩኒቨርስቲው የኮንስትራክሽንና ሜንቴናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደንበሹ ኒኤሬ ሰሞኑን እንደገለጹት ግንባታ በ2004 የተጀመረው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ ህንጻ የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንበታ 164 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ነው ። በመገንባት ላየ ያለዉ ህንጻ በርካታ የመማሪያ ክፍሎች፣ የሌክቸር አዳራሽ፣ ቤተሙከራ፣ ቢሮዎች፣ የተማሪዎች መዝናኛዎችን የያዘ መሆኑን አስታዉቀዋል ። በሁለተኛው ምዕራፍ 251 ሚሊዮን ብር የተመደበለት የተማሪዎች ማደሪያና መስተንግዶ፣ የመመገቢያ አዳራሽ፣ የቴክኖሎጂ ላብራቶሪ ጨምሮ ለሌሎች ግንባታዎች እንደሚካሄዱ አስረድተዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው ዋና ግቢ የሚገነባዉ ህንጻ የአካል ጉዳተኞች መወጣጫና መመላለሻዎችን ከግምት የሚያስገባ ሲሆን ከአጠቃላይ ግንባታዉ እስከአሁን ከ30 በመቶ በላይ መከናወኑን ጠቁመዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ በ2007 የስራ ዘመን ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ በመደበኛነት ብቻ 15ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተማር አቅም እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ የኢንስቲትዩቱ መገንባት በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀገሪቱ የምትፈልጋቸውን የተማረ የሰው ሃይል በብዛትና በጥራት በማፍራት በተለይ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በየአመቱ የሚቀበላቸውን ተማሪዎች 70 በመቶ የሳይንስናቴክኖሎጂ ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ግብ በማሳካት ከፍተኛ አስተዋጾኦ እንዳለው አቶ ደንበሹ አስረድተዋል፡፡ በዩኒቨርስቲው አምስቱም ካምፓሶች ኢንስቲትዩቱን ጨምሮ አሁን በመገንባት ላይ የሚገኙትንና በ2006 ከሚጀመሩት ጋር ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው በርካታ ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩ ተመልክቷል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=10833&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር