የደቡብ ክልል ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ ሃላፊዎች ላይ ምርመራ ተጀመረ ;የክልሉ መንግስት በሲዳማ ዞን በበንሳ ወረዳ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁሮ ጡሙሮ የተሰኘ የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ያስጀምራል። ጨረታውን ደግሞ አቶ ተክለወልድ ማሞ የተሰኙ የውሃ ስራዎች ተቋራጭ ያሸንፋሉ ግለሰቦቹ 40 በመቶ ብቻ የተከናወነውን ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል በማለት ያለ አግባብ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረጋቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 9 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ  ምክትል ሃላፊ አቶ ውብሸት ጸጋዬን ጨምሮ አራት የተለያዩ የስራ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥርጥረው በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ተጀመረባቸው።
በደቡብ ክልል  ሰሞኑን የክልሉ ውሃ ሃብት ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊው አቶ ውብሸት ጸጋዬ ፣ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሃላፊው  ይገረመው ፋሲቆ ፣  የክፍያዎች ሃላፊው አቶ አቦሰጥ መብራቱ ፣ መሃንዲሱ አቶ ማገሳ ዮሃንስ እና ኮንትራክተሩ አቶ ተክለወልድ ማሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን  ኮሚሽነር ገበየሁ ገብሬ እንዳሉት ፥ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በመተባበር የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።
 የክልሉ መንግስት በሲዳማ ዞን በበንሳ ወረዳ ከ4 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሁሮ ጡሙሮ የተሰኘ የውሃ ፕሮጀክት ግንባታ  ያስጀምራል።
ጨረታውን ደግሞ አቶ ተክለወልድ ማሞ የተሰኙ የውሃ ስራዎች ተቋራጭ ያሸንፋሉ
ግለሰቦቹ 40 በመቶ ብቻ የተከናወነውን ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል በማለት ያለ አግባብ ክፍያ እንዲፈጸም በማድረጋቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።
 ግለሰቦቹ  በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እንዲጀመርባቸው የሚያስችል በቂ ማስረጃ መገኘቱንም ነው አቶ ገበየሁ የተናገሩት።
የፈደራል ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን የጸረ ሙስና ትግሉን ሃገራዊ ለማድረግ ከክልሎች ጋር በመቀናጀት በጋራ እየሰራ ነው የሚገኘው።
በፈደራል ተፈጽሞ መሸሸጊያውን ክልል ሊያደርግ  የሚሞክር የሙስና ተግባር መግቢያ እንዲያጣ ለማድረግ ይህ የፌደራልና የክልሎች ቅንጅታዊ ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ነው እየተነገረ ያለው።
በፌደራል ደረጃ በቅርቡ በገቢዎችና ጉሙሩክ እንዲሁም በኢትዮዽያ ኤሌክትሪክ  ሃይል ኮርፖሬሽን የሙስና ወንጀሎችን  የማጋለጡ ስራ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ተወስኖ እንዳይቀር ይህ መድረክ  በሌላ በኩል ያስገኘው ጥቅም ነው።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር