በሀዋሳ ሀይቅ በጉማሬ ጥቃት የደረሰበት የ15 አመቱ ታዳጊ ለህልፈት ተዳረገ

አዲስ አበባ ፣ሀምሌ 25 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐዋሳ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዳጋ ቀበሌ ውስጥ የ15 አመት እድሜ ያለው የ9ኛ ክፍል ተማሪ ከትናንት በስቲያ 3 ከ30 ላይ ሃዋሳ ሃይቅ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል።

ሟች ሃይቅ ውስጥ በመዋኘት ላይ እያለ አጠገቡ የነበረች አንድ ጉማሬ ግራ እግሩን በመንከስ እና አንስታ በመወርወር ህይዎቱ  እንዲያልፍ አድርጋዋለች።
ከሃይቁ ውጭ ሆነው ሁኔታውን ሲከታተሉ የነበሩ ጓደኞቹ ለፖሊስ በመናገራቸው ፖሊስ ደርሶ ጉዳዩን እንዲመለከት አድርገዋል።
ኢንስፔክተር ሳሙኤል ኩማ እንዳሉት  ፥ በአዲስ ከተማ አካባቢ ጉማሬዎች ይበዛሉ ፤ ይሁን እንጅ የጉማሬዎቹ ባህሪ ስለማይታወቅ ሰዎች ባይነኳቸው ይመረጣልም ነው ያሉት።
በሀይቁ ላይ ጉማሬ መሰል አደጋ ሲያደርስ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የጠቀሱት ኢንስፔክተር ሳሙኤል ፥ ጉማሬዎቹ በሃዋሳ ሃይቅ ላይ ብቅ የሚሉበት የራሳቸው የሆነ ጊዜ እንዳላቸው እና  በተለይ ጤዛ የመላስ ባህሪ ስላላቸው እና ቁስለት ሲኖርባቸውም ውጭ ስለሚያገግሙ ሰዎች ባይቀርቧቸው የተሻለ ነው በማለት መክረዋል ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር