የ10ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ለማየት ያጋጠመው ችግር እየተቃለለ ነው

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ 2005 ዓም የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት 11/12/2005 ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ይፋ መሆኑን አስታውቆ ነበር፡፡ 
ተፈታኞቹ ውጤታቸውን በተቋሙ ድረ ገፅ www.nae.gov.et እና በተንቀሳቃሽ ስልካቸውአጭር መልዕክት በመላከ ማወቅ እንደሚችሉ ገልፆ ነበር፡፡
ይሁንና የተወሰኑ ተጠቃሚዎች መረጃውን ያገኙ ቢሆንም በርካታ ተጠቃሚዎች ግን ወደ ኢሬቴድ በመደወል የተባለውን መረጃ ለማግኘት እንደተቸገሩ ነግረውናል፡፡ በጉዳይ ላይ ማብራሪያ የጠየቅናቸው የኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ችግሩ ሁሉንም ጠያቂዎች ባንድ ላይ ማስተናገድ ባለመቻሉ የተፈጠረ ነው ብለዋል፡፡
ሃላፊው እንዳሉት አሁን በአጭር የስልክ መልዕክት መረጃውን የሚያደርሰው የመረጃ ቋት በአንድ ደቂቃ ማስተናገድ የሚችለው ከ5ሺ እስከ 7ሺ ጥያቄዎችን ነው፡፡ ይሁንና ወደ መረጃ ቋቱ ከ 20ሺ በላይ ጥያቄዎች በአንድ ደቂቃ ዉስጥ ይደርሳሉ፡፡ ለአንድ ተማሪ ዉጤት ከ20 እስከ 30 ሰዎች ያክል ጥያቄ ማቅረባቸው ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ብለዋል ሃላፊው፡፡
ይህም በማዕከሉ ላይ መጨናነቅ በመፍጠሩ በርካታ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን እንዳላገኙ ተረድተናል ብለዋል፡፡ በድረ ገፅ የሚጠቀሙ ያጋጠማቸው ችግር አሁን ሙሉ በሙሉ የተቃለለ በመሆኑ ተፈታኞቹ ውጤታቸውን በተቋሙ ድረ ገፅ www.nae.gov.et አሁን ጀምረው ማየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
በአጭር ስልክ መልዕክት የሚጠቀሙ መጨናነቁ አሁን እየተቃለለ በመሆኑ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቀዋል፡፡ የአጭር መልዕክቱን  rtn ብለው ከፃፉ በኋላ የመፈተኛ  የመለያ ቁጥርበማስገባት ወደ 8181 በመላክ ማወቅ ይቻላል፡፡
አሁንም ግን ድረ ገፁ በመጨናነቁ ፈጣን አገልግሎት መስጠት ያለመቻሉን ተመልክተናል፡፡
2005 የትምህርት ዘመን ለፈተና ከቀረቡ 548,138 ተማሪዎች ውስጥ 2 ነጥብና ከዛ በላይያመጡ ተማሪዎቸ 70 በመቶ ናቸው፡፡ ለፈተና ከተቀመጡት ተማሪዎች  ከአምናው ተመሳሳይወቅት  ጋር ሲነፃፀር በመቶ የውጤት ብልጫ አሳይቷል፡፡
ለፈተና ከተቀመጡት አጠቃላይ ተፈተኞች ውስጥ 256,588 ሴት ተማሪዎች መሆናቸው ነውየተገለፀው፡፡
የተማሪዎች ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል አያሳየ ሲሆንመንግስት ለትምህርት ጥራት የሰጠውንልዩ ትኩረት ያሳያል ሲሉ የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር ዘሪሁን ዱሬሳ ተናግረዋል፡፡ የመሰናዶመግቢያ  ነጥብም እስከ 13 ባሉት ቀናት ውስጥ ይታወቃል ብለዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር