የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ተጀመረ የክልሉን ርዕስ መስተዳደር ሹመት ጽድቋል

ከሃዋሳ በደረሰን ዜና መሰረት የቀደሞውን የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ተክተው ኣቶ  ደሴ ዳልኬ ተሹመዋል። የኣቶ ደሴ ዳልኬ መሾም ሲዳማ በደቡብ ክልል መንግስት ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ሚና ትልቅነት የሚያሳይ እና በክልሉ ያለው የፖለቲካ መሪነት ቀጣይነት ያረጋገጠ ነው ተብለዋል።

ሲዳማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ተዋቅሮ የነበሩት ብሄርና ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ወደውም ሆነ ሳይወዱ በኣንድ ክልል ከተጠቃለሉ ጊዜ ጀምሮ ሲዳማ የክልሉን ፖለቲካ በበላይነት መምራቱን ቀጥሎበታል። እስከ ኣሁን የደቡብ ክልልን ከመሩት እና በመምራት ካሉት ኣራት ርዕስ መስተዳደሮች መካከል ሶስቱ ከሲዳማ ናቸው።

ኣቶ ደሴ ዳልኬ ባለፉት ኣስራ ሁለት ኣመታት በሲዳማ ዞን ውስጥ በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ የሰሩ እና ላለፉት ሶስት ዓመታት የሣይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የቆዩ ናቸው።


የኣቶ ደሴ ዳልኬ ወደ ደቡብ ክልል ተመልሰው መምጣት ለሲዳማ ያለው እድምታ ምን እንደሆነ ለጊዜው ግልጽ ባይሆንም በሲዳማ ዘንድ የተደበላለው ስሜት ፈጥሯል። ኣቶ ደሴ ዳልኬ በሲዳማ ህዝብ ዘንድ በየጊዜው እየተነሳ የቆየውን የሲዳማ ክልል ጥያቄን በተመለከተ የሚኖራቸውን ኣቋም ከዚህ በፊት ከነበሩት የክልሉ መሪዎች የተለየ እንደማይሆን የተገመተ ሲሆን ለክልል ጥያቄው ኣዎንታዊ ምላሽ እንዲሰጥ የሚያደርጉ ከሆነ የሲዳማ ህዝብ ድጋፊ እና ፍቅር ሊያገኑ ይችላሉ ተብሏል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር