የቀድሞው የሃዋሳ ከተማ ስራ ኣስኪያጂ የነበሩት እና በኃላ ላይ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሆኑትን ኣቶ ተፈሪ ፍቅሬ ጨምሮ ሌሎች ሁለት ዳይሬክተሮች በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው ከስራ ሃላፊነታቸው ተነሱ::

የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር አቶ ተፈሪ ፍቅሬና ሁለት ምክትል ዳይሬክተሮች በኪራይ ሰብሳቢነት ተገምግመው ከስራ ሃላፊነታቸው እንደተነሱ ተገለፀ፡፡

ተጠሪነቱ ለስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሆነው የቤቶች ኤጀንሲ ከትላንት በስቲያ ሶስቱን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከሥራ ሃላፊነታቸው ያነሳው በተለያየ ደረጃ ግምገማ ከተካሄደ በኋላ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽንም ከአንድ ዓመት በላይ በሥራ ሃላፊዎቹ ላይ ምርመራ ሲያደርግ እንደቆየ የጠቀሱ ምንጮች፤ ሃላፊዎቹ በኪራይ ሰብሳቢነትና ሃላፊነትን በአግባቡ ባለመወጣት ተገምግመው ነው ከሥራ ሃላፊነታቸው የተነሱት ብለዋል።
http://dezetube.com/article_read.php?a=451

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር