አቶ ደሴ ዳልኬ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆኑ

ሃዋሳ ሐምሌ 06/2005 የክልሉ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ መደበኛ ጉባኤ አቶ ደሴ ዳልኬን የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት ርእሰ መስተዳድር አድርጎ መረጠ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ ከቀድሞው ርእስ መስተዳድር ከአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የክልሉን መንግስት ቁልፍ በመረከብ በይፋ ስራ ጀምረዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ደሴ ዳልኬ እንዳስገነዘቡት ክልሉ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማእከል በመሆኑ ለእኩል የልማት ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ፡፡ መላ የክልሉን ሕዝብ በአንድነት ለማጠናከር የተጀመሩ የልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ የሲዳማ ብሔር ተወላጅ ሲሆኑ የትምህርት ዝግጅታቸው በስነ ህይወት ሳይንስ የመጀመሪያና በለውጥ አመራር ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውና ከወረዳ ጀምሮ እስከ ፌዴራል በተለያየ የሃላፊነት እርከን ያገለገሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ የቀድሞው ርእስ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለፉት ስምንት አመታት በክልሉ ልማትና መልካም አስተዳደር እንደዲሰፍ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የክልሉ ምክር ቤት አባላትና ድርጅቱ እውቅና ሰጥቷቸዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=9613&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር