በክልሉ የተጀመሩ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሰርዓት ግንባታ ለማጠናከር ትኩረት ይሰጣል

አዋሳ ሐምሌ 07/2005 በደቡብ ክልል የተጀመሩ የልማት፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሰርዓት ግንባታ በማጠናከር ፍትሃዊ የልማት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አዲሱ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግስት የ2006 በበጀት ዓመት እቅድ ለምክር ቤቱ አባላት አቅርበዋል፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ባለፉት ሶስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በየዘርፉ ታቅደው ያልተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር በመገምገምና መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት በቀጣይ በሁሉም የልማት መስኮች ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወንና የህብረተሰቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርብ ይደረጋል፡፡ በርብርቡ የሚካሄደው መንግስትና በድርጅት የቅርብ አመራር ሰጭነት፣ በባለሙያው ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በህብረተሰቡ የተሟላ ተሳትፈፎና በቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በየስራ ዘርፉ የግንባር ቀደም ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት በገጠርም ሆነ በከተማ ድህነትን ለማስወገድ በሚያስችል መልኩ የጋራ ጥረት እንደሚደረግ አመልክተዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት በክልሉ ታቅደው ላልተከናወኑ ተግባራት በርካታ ምክንያቶች ቢኖሩም የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር፣ የአስፈፃሚውና የፈፃሚው አቅም ውስንነት፣ቴክኖሎጂውን በተሟላ ሁኔታ ያለመጠቀም በዋናነት እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡ እነዚህን ጉድለቶችን ለመቅረፍ የመንግስት፣ የድርጅትና የዝህብ ክንፎችን አቅም አቀናጅቶ በየደረጃው የልማት ሰራዊት በመገንባት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድና የሚሌኒየም የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚከናወኑ ገልፀዋል፡፡ በግብርናው መስክ አርሶአደሩ የተሻሻሉ ቴክኖሎጅዎችን ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ ርብርብ ይደረጋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በመስኖ ፣በበልግና በመኸር ከ2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች በማልማት ከ86 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡ በበጀት ዓመቱ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የገበያን ፍላጎትና የተሻለ ዋጋ የሚያስገኙ ምርቶች በማምረት ላይ መሰረት ያደረገ ለውጭ ገበያና ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ የሰብል ልማት ስራዎች ተለይቶ በአከባቢና በቤተሰብ ደረጃ የምርታማነት ጭማሪ እንዲመጣ እንደሚሠራም አስረድተዋል፡፡ ስለሆነም የግንዘቤና የክህሎት ስልጠና የመስጠት፣ የተሻሻሉ አሰራሮች እንዲተገበሩ የማድረግ፣ ግብአትን በብዛትና በጥራት ማቅረብና አጠቃቀምን የማሻሻል ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ አስታወቀዋል፡፡ በገጠር የወጣቶች ስራ አጥነት ችግሮችን ዘላቂነት ባለው መልኩ ለመቅረፍ 310 ሺስራ አጥ ወጣቶችን የመለየትና ከእነዚህም 170 ሸ የሚሆኑት በመረጡት የስራ መስኮች ላይ በማህበርና በቡድን በማደራጀት የስልጠና፣ የብድር፣ እንዲሁም የግብአትና የምርት ገበያ ትስስር የመፍጠር ስራዎች እንደሚሰሩ ጠቁመዋል፡፡ በክልሉ የንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ በበጀት ዓመቱ ከ1ሺ 800 በላይ አዲስና ነባር የውሃ ተቋማት ግንባታና ጥገና በማድረግ በገጠርና በከተማ ከ5 ሚሊዮን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ሽፋኑን በገጠር 81 በከተማ 91 ነጥብ 13 በመቶ ለማድረስ ጥረቱ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ በክልሉ የሚሰበሰበውን ገቢ በማሳደግ በኩል በክልሉ የሚከናወኑ ሁሉንም የልማት ስራዎች ለማፋጠንና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እንዲሁም በበጀት አቅም ክልሉ ራሱን ለመደጎም ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሚሰበስብ ገልፀዋል፡፡ በክልሉ በበጀት ዓመቱ የታቀዱትን ስራዎች ተግባራዊ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኙ አካላት በተለይ የምክር ቤቱ አባላት፣አመራሩና ባለሙያው የላቀ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው ርዕሰ መስተዳድሩ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=9679

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር