ሲዳማን ጨምሮ ከመላው ኣገሪቱ የተወጣጡ የህብረት ስራ ማህበራት የተሳተፉበት ጉባሴ ሰሞኑን በኣዋሳ ተካህዷል

አዋሳ ሐምሌ 04/2005 በግብርና የህብረት ስራ ልማት ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት መንግስት በሰጠው ትኩረት ሀገር አቀፍ ስተራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የፌዴራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡ በሀዋሳ ከተማ ሰሞኑን በተከበረው ሀገር አቀፍ የህብረት ስራ ቀን በዓል ላይ የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው እንደገለጹት ግብርና ለኢትዮጵያ እድገት መሰረት፣ ለውጪ ምንዛሬና የአብዛኛው መተዳደሪያ ገቢ ምንጭ መሰረት በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ ስለሆነም ስትራቴጂው የህብረት ስራ ማህበራት ከተለምዶ አሰራር ተላቀው በአደረጃጀት፣ በአሰራር ስርአታቸውና በሰው ሀይላቸው ይበልጥ ጎልበተው የአርሶና አርበቶአደሩን ምርትና ገበያ ማሻሻል ነው ብለዋል፡፡ የግብርና ህብረት ስራ ዘርፍ ልማት ስትራቴጂ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ካውንስል ባለፈው አመት ጸድቆ በ2005 በጀት አመት መተግበር ጀምሯል ብለዋል፡፡ ስትራቴጂው ቅድሚያ መተግበር የጀመረው በትግራይ ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በአማራ ብሄራዊ ክልሎች የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ተግባራዊ ባደረጉ የተመረጡ ወረዳዎች እንደሆነም ገልጸዋል፡፡ በስትራቴጂው ትግበራ የመጀመሪያው ዓመት ከተመዘገቡ ውጤቶች መካከል የህብረት ስራ ማህበራት የላቀ ዕውቅና የመስጠትና የልቀት ማዕከል የማቋቋም ስራ መጀመሩ፣በአራቱ ክልሎች ለሚገኙ ለ9 የህብረት ስራ ዩኔየኖች ከአባላቶቻቸው ምርት በማሰባሰብ ግብይት እንዲፈጽሙ ከ354 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር እንዲያገኙ መደረጉ እንደሚገኝበት ተናግረዋል፡፡ ከዚህም ሌላ የማህበራት ግብይት ሰንሰለት ለማሰጠር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ በሰሊጥ፣ በቡና፣ በስንዴ፣ በጤፍ በገብስና በሽምብራ ግብይት የተሰማሩ የህብረት ስራ ዩኒየኖችና የህብረት ስራ ማስፋፊያ አመራር አካላት ወደ ግብይት የሚያስገባ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡ አራት ዩኒየኖች 18 ሺ ኩንታል ሰሊጥ ለውጪ ገበያ እንዲልኩ በተደረገው ድጋፍ ከ3 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት ተችሏል፡፡ የግብይት መሰረተ ልማት ለማሻሻል ከዩ ኤስ ኤድ በተገኘ ድጋፍ በሁለት ክልሎች ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እያንዳንዳቸው 5 ሺ ኩንታል ሰሊጥ የሚይዙ አራት መጋዘኖች በመገንባት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ የግብርና ህብረት ስራ ማሀበራት ተግባራትም በሚያገኙት ድጋፍ ተጠናክረው የምርት ግብአት ግዥና ስርጭት፣ የኤክስቴንሽን አገልግሎት፣ የምርት ግብይት እሴት መጨመሩን ማካተት፣ የትርፍ ክፍፍል፣ ሁለገብ አገልግሎትና ሌሎችም ስራዎች በማካሄድ ለአባላትና ለየአካባቢያቸው ህብረተሰብ መስጠት እንደሚገኙበት አመልክተዋል፡፡ ስትራቴጂው ለእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ብሎም ሀገሪቱ በ2017 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማስለፍየተያዘውን ራዕይ ለማሳካት የግብርና ህብረት ስራ ማህበራት ህዝብን በማነቃነቅ የሚኖራቸውን ከፍተኛ ሚና ለማጎልበት እንደሚስችልም አሰረድተዋል፡፡ የበሀገሪቱን ከ6 ሚሊዮን በላይ አባለትን ያቀፉ ከ43 ሺ በላይ መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራትና ከ1ነጥብ 5 ቢሊዮን በላይ ካፒታል ያፈሩ አንዲሁም 293 የህብረት ስራ ዩኒየኖች ተቋቁመው የአባላትና የአካባቢያቸውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች እየፈቱ እንደሚገኙ ተገልጻል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=9524&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር