በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ ተማሪዎችና ወላጆችን በማሳተፍ ተግባራዊ የሆነዉ የማስተማር ዘዴ ዉጤት እያስገኘ ነዉ

አዋሳ ግንቦት 13/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በትምህርት ስራው ላይ ተማሪዎችና ወላጆችን በማሳተፍ የተከናወነዉ ተግባር በተማሪዎች ውጤት ላይ ለውጥ ማምጣት መቻሉን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አዝመራ አመኑ በወረዳው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በትምህርት ቤቶች ምምህራንና ተማሪዎች ዕቅድ በማውጣትና ተግባራዊ በማድረግ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ። በወረዳው በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችን መሰረት በማድረግ ትምህርት ቤቶች ለትምህርት ስራው ምቹ እንዲሆኑ የተደረገዉ ጥረትም ለዉጤቱ መገኘት አስተዋጽኦ ማድረጉንም ገልጠዋል ። ለአራተኛና ስምንተኛ ክፍል የቲቶሪያል ማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት እንዲሁም ከአስረኛ ክፍል ጀምሮ ላሉት ተማሪዎች ከመደበኛው የትምህርት ሰዓት በተጨማሪ ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር ማታ ማታ የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል። በወረዳው የሴት ተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎና ውጤት ለማሻሻል ሴት ተማሪዎች ተለይተው ድጋፍ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑን በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን በቡድን በማደራጀት እርስ በእርስ ውድድር እንዲያደርጉና ተማሪዎች የልምድ ልውውጥ እንዲያገኙም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ለአራተኛና ስምንተኛ ክፍል ወረዳ አቀፍ ፈተና አዘጋጅቶ በመፈተን ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ የማካካሻ ትምህርት በመስጠት ለክልላዊ ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የማድረግስራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ አዝመራ ገልጸዋል። የሸበዲኖ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ጋቤራ በበኩላቸው በወረዳው በሚገኙ 35 ቀበሌዎች የወላጅ መምህራን ህብረትን በማጠናከርና በየደረጃው በተዋቀሩ የልማት ቡድኖችና አንድ ለአምስት ትስስሮች አማካኝነት በትምህርት ስራ ህብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳታፊ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል። የወረዳው አስተዳደር የትምህርት ስራው ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ስራ ውጤታማ እንዲሆን ከወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። በወረዳው የለኩ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪ ማቲዎስ ጴጥሮስና ተማሪ በረከት ጌታቸው እንደገለጹት በትምህርት ቤቶች ባለፉት ሁለት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራት በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል ያመጣ መሆኑን ገልጸዋል። እንደ ተማሪዎቹ ገለጻ በመደበኛ የትምህርት ሰዓት በትምህርት ቤቱ ከሚያገኙት ትምህርት በተጨማሪ ከእሁድ በስተቀር በተቀሩት ቀናት ማታ ማታ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠን ነው ብለዋል። በመምሀራንና በወላጆችቻቸው በሚደረግላቸው ድጋፍ በመታገዝ አምና በአስረኛ ክፍል ፈተና ያስመዘገቡት ከፍተኛ ውጤት በወረዳው ለትምህርት ስራ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። በፈተናውም ተማሪ ጴጥሮስ የተፈተናቸውን 10 ትምህርቶች ኤ ያመጣ ሲሆን ተማሪ በረከት ከ10 ዘጠኙን ኤ አንዱን ቢ በማምጣት በከፍተኛ ዉጤት ማለፍ መቻላቸው ማሳያ ነው ብለዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=8011&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር