ሰሞኑን በሸቤዲኖ ወረዳ በላኮ ከተማ በተነሳው እሳት ግምቱ ሁለት ሚሊዮን የሚገመት ንብረት መውደሙ ተነግሯል

ከምሽቱ ኣምስት ሰዓት ኣካባቢ ከኣንድ መኖሪያ ቤት ተነሳ የተባለው እሳት በኣካባቢው የነበሩት ወደ 12 የሚሆኑ የንግድ ቤቶችን ያቃጠለ ሲሆን ከተቃጠሉት የንግድ ቤቶች መካከል የምግብ ቤቶች፤ የሸቀጣሸቀጥ መደብሮች፤ የመድሃኒት ቤት፤ የህንጻ መሳሪያ መሸጫን የመሳሰሉት ይገኙበታል።
ቃጠሎው ያወደማቸውን ቤቶች ተዘዋውረው የጎበኙት የዞኑ ካፍተኛ ባለስልጣናት ንብረታቸውን በእሳት ላጡ ለከተማዋ ነዋሪዎች መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግ መናገራቸው ተሰምቷል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር