ሠራተኛው ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ጠንክሮ መሥራት አለበት

አዋሳ ግንቦት 05/2005 ሠራተኛው የስራ ባህሉን በማሻሻል በታታሪነት በመስራት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ጠንክሮ መሥራት እንዳለበት ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማብራት ኮንፌዴሬሽን 50 ዓመት የወርቅ ኢዩቤል ክብረ በዓሉን ትላንት በሀዋሳ ከተማ በፓናል ውይይት አክብሯል፡፡ የርዕሰ መስተዳድሩ ስተዳድሩ ተወካይ አቶ ታመነ ተሰማ ትናንት በፓናል ውይይቱ መክፈቻ ላይ እንደገለጹት ሠራተኛው የስራ ባህሉን በማሻሻል በታታሪነትና በዓላማ ፅናት በመስራት በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን ጉልበትና ዕውቀቱን አቀናጅቶ ጠንክሮ መሥራት አለበት፡፡ ኢሠማኮ የግል ተቀጣሪ ሰራተኞች የማህበራዊ ዋስትና እንዲያገኙና ሀገሪቱ ከግብር መር ወደ እንዱስትሪ መር እንደድትሸጋገር በማድረግ በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ከሳሁን ፎሎ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ሰራተኞች ያበረከቱአቸውን ሀገራዊ አስተዋጽኦ የመዘከር፣ አሰሪና ሰራተኛ ተግባብተው በአንድ መንፈስ እንዲንቀሳቀሱ የማነሳሳትና ሁሉም ወገን ተጠቃሚ የሚሆንበት ምቹ ሁኔታን የመፍጠር አላማ ያነገበ ነው ብለዋል፡፡ ሠራተኛው ጉልበትና ዕውቀቱን ሳይቆጥብ የህዳሴውን ግድብ ከግብ ለማድረስ እያደረገ ያለው ያላሰለሰ ጥረት የሚያኮራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በበዓሉ ላይ በሀዋሳና አካባቢዋ የሚገኙ ሰራተኞች አሰሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡
Sources: Ena

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር