አርባምንጭ ከነማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መብራት ኃይልና ሲዳማ ቡና አሸነፉ


ዛሬ ሚያዝያ 23/2005 ዓ.ም በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች አምስት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
አርባምንጭ ከነማ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ መብራት ኃይል እና ሲዳማ ቡና ድል ሲቀናቸው ሙገር ሲሚንቶና መከላከያ ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ስታድየም የተካሄደው የውኃ ስራ እና የአርባ ምንጭ ከነማ ጨዋታ በአርባምንጭ ከነማ 6 ለ 3 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የአርባምንጩ ገብረሚካዔል ያቆብ ሀትሪክ ሰርቷል፡፡
በጨዋታው አስደንጋጭ ጉዳት ያጋጠመው የአርባምንጩ እምሻው ካሱ ሆስፕታል ከተወሰደ በኋላ በደህና ጤንነት ላይ ቡድኑን መቀላቀል ችሏል፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታድየም ሀረር ቢራን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ቡና 5 ለ 1 አሸንፏል፡፡ ሲዳማ ቡና አዳማ ከነማን አስተናግዶ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ረቷል፡፡
ወደ አሰላ ተጉዞ ሙገር ሲሚንቶን የገጠመው መከላከያ ያለምንም ጎል ተለያይቶ ነጥብ ሲጥል ሙገር ሲሚንቶ ከወራጅ ቀጠና የሚርቅበትን ነጥብ አጠናክሯል፡፡
በአዲስ አበባ ስታድየም በ11 ሰዓት በተደረገ ጨዋታ መብራት ኃይል ሀዋሳ ከነማን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ 
ሊጉን ደደቢት በ39 ነጥብ ሲመራ ኢትዮጵያ ቡና በ33፣ መብራት ኃይል እና ሀዋሳ ከነማ በ30፣ መከላከያ በ29፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ25 ነጥቦች ይከተላል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር