በተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮግራም የአካባቢያዊ የዘር ቢዝነስ ፕሮጀክት 3 (LSB) እንቅስቃሴ

ዶ/ር ሁሴን መሀመድ እባላለሁ፤በመምህርነት (በአሶሼትፕሮፌሰር ማዕረግ)፤ በዕፅዋት ማዳቀልና ዝርያ በማውጣት በአሁኑ ወቅት
ደግሞ ከመምህርነት በተጨማሪነት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ በመሆን እያገለገልኩ እገኛለሁ፡፡
የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት በጣም ሰፊ ፕሮግራም ነው፡ የዘር ዘርፍ ደግሞ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሳድጋሉ ከምንላቸው
አስፈላጊ ግብአቶች አንዱ ነው፡፡ በፕሮግራሙ ዋና አላማችን ዓለም አቀፍ ሰብል ዝርያ አባዢ ድርጅቶችን፤ ኢትዮጵያዊና
ገና በመጠናከር ላይ ያሉ የግል የዘር አባዢዎችን በተጨማሪም ተደራጅተው ዘርን አባዝተው የሚያቀርቡ የአርሶ አደር
ማህበራትንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አቀናጅቶ ለእድገታችን ማነቆ ሆኖ የቆየውን የዘር ዘርፍ ችግርን ለመፍታት ዘርን
በጥራትና በብዛት በማምረትና በማቅረብ በሀገራችን ውስጥ የጀመርነውን ፈጣን እድገት አስተማማኝ ለማድረግ ነው ፡፡
የዘር ዘርፍን ለማጠናከር የISSD ፕሮግራም የአርሶ አደር የዘር ብዜትና ግብይት ማህበራትና የግል የዘር አባዢዎችን
በመደገፍ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የተመሰከረለት ዘርን (Certified Seed) መጠበቅ፤ ጥራታቸውን የጠበቁ አራቢ፤ መስራችና
ቅድመመስራች ዘሮችን በምርምር ማዕከላት ደረጃ በጥራት እንዲመረቱና የአቅም ማጎልበት ስራንም ለመስራት መሰረታዊ
የዘር ዘርፍ ችግርን የሚያጤን ኮሚቴ (Core Group) ከተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮግራም፤ ከክልል ግብርና ቢሮ፤
መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች (NGO)፤ ከደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅትና፤ ከደቡብ ግብርና ምርምር ማዕከል በተወጣጡ
አባላት ተቋቁሞ በዘርፉ ያሉትን ችግሮች ነቅሶ በማውጣት ለእነኚህ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት እየሰራን እንገኛለን፡፡
ቀደም ብሎ የዘርፉ መሰረታዊ ችግር የነበረው የአራቢ እና ቅድመ መስራች ዘርን በጥራትና በብዛት የማምረት ጉዳይን
የደቡብ ግብርና ማዕከል በአሁኑ ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ በፊት ብዙም ትኩረት ያልተሰጠበት የምርምር
ማዕከሉን የማጠናከር ጉዳይም አሁን በቁሳቁስና በሰው ሐይል የማደራጀቱን ጉዳይ ላይ በስፋት እየሰራን እንገኛለን፡፡
በሀገር አቀፍ ደረጃ በፖሊሲ ዙሪያ ያሉ ማነቆዎችን በመለየት ከመንግስት አካላትና ከፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ጋር በመሆን
የISSD ፕሮግራም አጋርነትን በማጠናከርና የዘርፉን ባለድርሻ አካላት በማቀራረብ የዘር ህጉ እንዲሻሻል በማድረጉ ስራ ላይ
ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ፡፡
በአቅም ግንባታ ዘርፍ ላይም ፕሮግራማችን በሀገር አቀፍ ደረጃ በዋነኛነት ከዩኒቨርስቲዎች ጋር በመቀናጀት ይሰራል ፕሮግራማችን
በመጀመሪያው ዙር ከ2009-2011 ባለው ጊዜ ከ40 በላይ የማስተርስ ተማሪዎችን በመደገፍ በዘር ዘርፉ ላይ ያሉትን ችግሮች
ነቅሰው በማውጣት ሳይንሳዊ መፍትሄ እንዲያቀርቡ አድርጓል፡፡ በሁለተኛው የፕሮግራሙ ምዕራፍ ደግሞ 4የዶክትሬት ዲግሪ
ትምህርት እድልን ሰጥቶ የአቅም ግንባታ ስራውን ቀጥሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአለም ላይ በዘር ዘርፉ ውስጥ ስኬታማ የሚባሉ
ሀገሮችን ልምድ ወደ ሀገራችን ለማምጣት ከግብርና ቢሮ፤ ከምርምር ማዕከላት፣ ከዘር አባዢዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተለያዩ
ባለሙያዎችን ወደ ውጪ ሀገር በመውሰድ ልምዶችን ቀስመው በኛ ሀገር አግባብ በመተርጎም እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራን ሰርቷል፡፡
በዘር ግብይት ዘርፍም ቀደም ብሎ የነበረውን ባለ ረጅም ሰንሰለት የግብይት ሂደት ለማሻሻል የቀጥተኛ
የዘር ግብይት ሂደትን በማስተዋወቅ ጊዜንና ጉልበትን ቆጥቦ ተጠያቂነትን በመፍጠር ዘርን በቀጥታ ለአርሶ
አደሩ የማድረስ ስራን በሙከራ ደረጃ እየሰራን እንገኛለን እስከ አሁንም አመርቂ ውጤቶች አግኝተናል፡፡
በአጠቃላይ የተቀናጀ የዘር ዘርፍ ልማት ፕሮግራም ሁሉን አቀፍ የሆነና የዘር ዘርፉ ማነቆ የሆኑበትን ችግሮች ከስር እስከ ላይ ድረስ
ለመቅረፍ ቆርጦ የተነሳ ፕሮግራም ነው፡፡ በመጨረሻም ድር ቢያብር አንበሳ ያስር ነውና ጣት በመጠቋቆም ሳይሆን በመተባበር፤
ችግሮችን ነቅሶ በማውጣትና በመወያየት ይህንን ለእድገታችን ትልቅ አስተዋፆ የሚያደርግ ዘርፍ መደገፍ ይጠበቅብናል ፡፡

Read more:http://www.hu.edu.et/hu/Downloads/Pdf/issd2.pdf

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር