ብሄራዊ የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ነገ ይጀመራል_ መልካም እድል ለሲዴ ልጆች
አዲስአበባ፣ ግንቦት 20፣ 2005(ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር አቀፍ የትምህርትምዝና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ደግሞ አጠቃላይ ዝግጅቴን አጠናቅቄለው ብሏል።
ኤጀንሲው ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳለው ነገ በሚጀመረው ፈተና 785 ሺ 183 ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።
ከዚህ ውስጥም 349 ሺ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ 1ሺ 347 የመፈተኛ ጣቢያዎች ዝግጁ የሆኑ ሲሆን ከ29ሺ 800 በላይ የፈተና ጣቢያ ሀላፊዎች፣ ሱፐር ቫይዘሮች እና ፈታኞች መዘጋጀታቸው ተግልጿ።
በዘንድሮ ሀገር አቀፍ ፈተና በተለየ ሁኔታ ኩረጃን ለመከላከል ሲባል ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ወደ መፈተኛ ጣቢያ ይዞ መምጣት ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ኤጀንሲው አሳስቧል።
ይህን በሚያደርጉ ተማሪዎች ላይ ከፈተና እስከ መሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ታውቋል።
በሌላ በኩል የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከግንቦተ 26 እስከ 29 ድረስ ይሰጣል።
ለዚህ ምዘናም ከ171ሺ 300 በላይ ተማሪዎች ፈተናውን ይወስዳሉ።
Comments
Post a Comment