የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ በምርምር የተገኙ የተለያዩ የምግብ ሰብል ዝርያዎችና ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና በማስተዋወቅ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡


የሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ በምርምር የተገኙ የተለያዩ የምግብ ሰብል ዝርያዎችና ቴክኖሎጂዎችን በማላመድና በማስተዋወቅ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ዩኒቨርሰቲው በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች 120 የምርምር ፕሮጀክቶችን እያካሄደ ነው፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሰቲ የምርምር ልማት ዳይሬክቶሬት የህብረተሰብ አገልግሎት ዘርፍ ባለሙያ አቶ ባዩ ቡንኩራ  ለኢ ዜ አ እንደገለጹት ዩኒቨርስቲው ሀዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ዞን በተመረጡ ስድስት ወረዳዎች የተቋቋሙ የቴክኖሎጂ መንደሮች አማካኝነት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡
በእነዚህ ወረዳዎች ከ360 በላይ ሞዴል አርሶ አደሮችን በማሳተፍ ካለፈው ክረምት ጀምሮ በዩኒቨርሰቲውና ሌሎች የምርምር ተቋማት የተገኙና ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የተለያዩ ስኳር ድንች(በአማካኝ በሄክታር 283 ኩንታል) ፣ የቦሎቄ፣ የቢራ ገብስ፣ የቦቆሎና ሌሎችም የሰብል ዝርያዎች በአርሶ አደሩ ጓሮና ማሳ ላይ ጭምር በማላመድና በማስተዋወቅ ተጠቃሚ እየሆኑ ናቸው፡፡
በአሁኑ ወቅት ካለው የበልግ እርሻና በመስኖ ጭምር በመጠቀም አዳደስ የሰብል ዝርያዎች አርሶ አደሩ እንዲጠቀም ከማስፋፋት በተጨማሪ ከእርሻ አያያዝና ከማዳባሪያ አጠቃቀም ጋር ያሉ ችግሮችን በመለየትና በተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና ለማስፋፋት ዩኒቨርስቲው ሰፋፊ ፕሮግራሞችን ዘርግቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ችግር ፈቺ የሆኑ 120 የምርምር ፕሮጀክቶችን በተለይም በግብርና፣ በምግብ ሳይንስ፣ በደን፣ በጤና፣ ትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በኢኮኖሚ፣ በተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ምርምር  እያካሄደ ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር