የኢትዮጵያ ምርጫ፤ ሰብአዊ መብትና ዉዝግብ


ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ብራስልስ ላይ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ከዓለም አቀፉ ድርጅት ሸላሚዎች ጋር አይግባባም፥ እንዲያዉም ይቃረናል።ከዋሽግተን ዲሲ የደረሰንን ዘገባ ከተከታተላችሁት፥ የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አርብ ማታ ይፋ ያደረገዉ ዓመታዊ ዘገባ ከጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም መግለጫ ጋር መቃረኑን አስተዉላችኋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኀላፊ፥---
ከተቃዋሚ ፓርቲ ባለሥልጣናት አንዱ፥ ---
የፖለቲካ ተንታኝ፥ ----
ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማይርያም ደሳለኝ፥---
የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሹም፥---
አይግባቡም።አይደማመጡም፥ ይቃረናሉም።እንዴት? ለምን? ላፍታ አብረን እንጠይቅ
------
የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች እንደዘገቡት፥ኢትዮጵያዉያን ሥደተኞች ለበርካታ አመታት እንደሚያደርጉ፥ እንደኖሩበት፥ከኖርዌ እስከ ዋሽግተን፥ ከአዳራሽ እስከ አደባባይ እንደተሰለፉ ያለፈዉ ሳምንት-ይሕን ሳምንት ተካ።ጥያቄዉ አንድም ብዙም ነዉ።መፈክሩ ግን ይቀነቀናል።ጥያቄዉ ይዥጎደጎዳል።ቅዳሜ፥-ስታቫንገር-ኖርዌ ተደገመ።

ቅዳሜ፥ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምናልባት አዲስ አበባ ይሆኑ ይሆናል።ከአራት ቀን በፊት ሮብ ግን ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ነበሩ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ከአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳት ከማርቲን ሹልስ ጋር ባደረጉት ዉይይት ከተነሱ ጉዳዮች የኢትዮጵያ መንግሥት የሠብአዊ መብት፥ የፕሬስ ነፃነት፥ የፍትሕ አያያዝ ዋናዎቹ ነበሩ።
 Addis Abeba, Äthiopien, Aufgenomen von unser Kori. ,Yohannes Gebereegziabher in Wahlurnen.
Titel Wahlen in Addis Abebe
Schlagworte Wahlurnen
Datum 21 04 2013
Fotograf Gebereegziabher,Yohannesድምፅ ሲሰጥ


ርዕሠ-መንበሩን ፓሪስ ፈረንሳይ ያደረገዉ የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፥ የሳይንስ እና የባሕል ድርጅት (UNESCO) የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ወንጀል በይግባኝ አምስት ዓመት እስራት ያስፈረደባትን አምደኛ፥ ፀሐፊና መምሕርት ርዕዮት ዓለሙን መሸለሙን ያስታወቀዉ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ-ማርያም እዚያዉ ምሥራቅ ፈረንሳይ እያሉ ነበሩ።ርዕዮት የተሸለመችበት ምክንያት፥-
ሽልማቱ እንዲሰጣት ከወሰኑት ዳኞች አንዱ፥-
በማግስቱ ሐሙስ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ብራስልስ ላይ እንዳሉት መንግሥታቸዉ ከዓለም አቀፉ ድርጅት ሸላሚዎች ጋር አይግባባም፥ እንዲያዉም ይቃረናል።ከዋሽግተን ዲሲ የደረሰንን ዘገባ ከተከታተላችሁት፥ የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አርብ ማታ ይፋ ያደረገዉ ዓመታዊ ዘገባ ከጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም መግለጫ ጋር መቃረኑን አስተዉላችኋል።እንቀጥል፥ አዲስ አበባ።

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም ከብራስልስ፥ በፓሪስ አድርገዉ አዲስ አበባ በገቡ በሳልስቱ፥ ከአዲስ አበባ ከመነሳታቸዉ በፊት የተጀመረዉ አካባቢያዊ ምርጫ ተጠናቀቀ።ዕሁድ።በምርጫዉ ዝግጅት እና ሒደት ገዢዉ ፓርቲ እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ-ባንድ ጎራ፥ ተቃዋሚዎቹ፥ በሌላ ጎራ ቆመዉ ይወዛገባሉ።እንዲያዉም ይቃረናሉ።

አቶ ይስማ ጅሩ ምርጫ ቦርድ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ናቸዉ።አቶ አስራት ጣሴ ሠላሳ ሰወስት ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያስተባብረዉ ጊዚያዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸዉ።ሠላሳ-ሰወስቱም ፓርቲዎች በምርጫዉ አልተሳተፉም።የምርጫ ዝግጅት ሒደቱንም ያወግዙታል።

አቶ ወድማገኘሁ ደነቀ፥-የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳትና የሰላሳ ሠወስቱ ፓርቲዎች አስተባባሪ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ናቸዉ።
 Addis Abeba, Äthiopien, Aufgenomen von unser Kori. ,Yohannes Gebereegziabher in Wahlurnen.
Titel Wahlen in Addis Abebe
Schlagworte Wahlurnen
Datum 21 04 2013
Fotograf Gebereegziabher,Yohannesምርጫ ጣቢያ
የምርጫ ቦርድ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ምክትል ኀላፊ ግን ሌላ ነዉ-የሚሉት።
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ጉዳይ ከተነሳ፥ የሰላሳ ሰወስቱ ፓርቲ ሰብሳቢ ያሉት አለ።
አቶ አስራት «ትክክል» ያሉት የሰላሳ ሰወስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አቋም በምርጫዉ ላለመሳተፍ መወሰናቸዉን ነበር።የዉሳኔያቸዉ ሰበብ ምክንያት «የዲሞክራሲ እጦት» ቢባል-የሚጠቃለል፥ ግን በአስራ-ስምንት ነጥቦች የተዘረዘሩ ቅድመ-ሁኔታዎች እንዲሟሉ ጠይቀዉ «ከገዢዉ ፓርቲና ከምርጫ ቦርድ መልስ በማጣታችን ነዉ» ባዮች ናቸዉ።አቶ ወንድማገኝ፥-

አንድ ሐገር፥ እንዲያዉም አንድ ከተማ ነዉ ያሉት፥እኩል ስለሚመለከታቸዉ አንድ ጉዳይ ነዉ የሚያወሩት ሥለ ምርጫ። ግን አይግባቡም።እንዲያዉም ይቃረናሉ።ይተዋወቁስ ይሆን?

ያለመግባባት፥ የመቃረን፥ ምናልባትም እየተዋወቁ የማይተዋወቁ የመምሰላቸዉ ሰበብ በርግጥ ብዙ ነዉ።ባለፈዉ ሳምንት ዕሁድ ተጀምሮ ትናንት ዕሁድ የተጠናቀቀዉ የአካባቢ ምርጫ በተገቢዉ መንገድ ተካሒዶ ቢሆን ኖር ግን ፍራንክፈርት-ጀርመን የሚኖሩት ኢትዮጵያዊዉ የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመመሥረት ለሚደረገዉ ተስፋ ወሳኝ በሆነ ነበር።

የገዢዉ ፓርቲ ተፅዕኖ፥ ወይም የተቃዋሚዎቹ ድክመት፥ ይባል ወይም ሌላ ባሁኑ ምርጫ መሆን የነበረበት አለመሆኑ፥ የሚታሰብ የሚፈለገዉን የዲሞክራሲ ተስፋ ጨርሶ ባያስቀረዉ እንኳ አርቆታል። እንደገና ዶክተር ለማ።

በ1997ቱ ብሔራዊ ምርጫ የፈነጠቀዉ ተስፋ በዉጤት ዉዝግብ፥ ባሳዛኝ ግጭት ተጨናጉላል።ያኔ ከእንግዲሕስ ብለን ነበር።በሁለተኛዉ ዓመት በተደረገዉ አካባቢያዊ ምርጫ እንዲሕ እንደዘንድሮዉ አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባለመሳተፋቸዉ በገዢዉ ፓርቲና በተባባሪዎቹ ድል ተጠናቅቋል።ያኔም ጠይቀን ነበር።የ2002ቱ ብሔራዊ ምርጫ ተቃዋሚዎች ተሳትፈዉም፥ በገዢዉ ፓርቲ የዘጠና ዘጠኝ ነጥብ ስድስት በመቶ ድል አብቅቷል።ያንኑ ጥያቄ አሰልሰን ጠይቀን ነበር።በዘንድሮዉም ምርጫ አዲስ ነገር የለም።አዲስ ጥያቄም የለንም።በ2007 ግን ሌላ ምርጫ አለ።አሮጌዉን ጥያቄ እንድገመዉ።ከእንግዲሕስ?
Pakistani journalists demonstrate against the attacks on the offices of the private Geo news channel and english daily The News International, in Islamabad on Friday, 16 March 2007. Windows were smashed in the lobby as police officers tried to interrupt transmission of violent scenes near the Supreme Court, where suspended chief justice Iftikhar Chaudhry stood before a panel of judges over allegations of misuse of office. EPA/NADEEM KHAWER +++(c) dpa - Report+++የፕረስ ነጻነት


የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሕዝብ ግኙነት ሐላፊ አቶ ይስማ ጅሩ መለሱ፥-እያሉ።የአንድነት ለዲሚክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ የሩቅም ቢሆን ተስፋ አላቸዉ፥-የሰላሳ ሰወስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተባባሪ አቶ አስራት ጣሴ ግን መጪዉን ምርጫ በቀቢፀ ተስፋ ነዉ የሚያዩት፥-።

ዶክተር ለማ፥ ይመክራሉ፥-ሰሚ ጆሮ ይገኝ ይሆን?

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር