ኢኮኖሚውና ቢዝነሱ ፈዟል! እናነቃቃው እንጂ!


ኢኮኖሚው ወድቋል፣ ሞቷል አይደለም እያልን ያለነው፡፡ ፈዟል ነው፡፡ በእውነት  ፈዟል፡፡ ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ፣ ተግባር ላይ ሲውሉና ሲሳኩም አገርን በእጅጉ የሚጠቅሙ፣ በሐሳብና በፍላጎት ብቻ ሳይሆን በተግባር ሥራቸው የተጀመረ ፕሮጀክቶች አሉ፡፡
ነገር ግን በሚያስተማምን ሁኔታ በቂ በጀት እያገኙ ያሉ ፕሮጀክቶች አይደሉም፡፡ ከውጭ ብድርና ዕርዳታ ከተገኘ ጥሩ፣ ካልተገኘ ደግሞ ራሳችን እንፈጽማቸዋለን ብለን የጀመርናቸው ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ በራስ ተማምኖ መጓዝን የመሰለ የለም፡፡ እዚህ ላይ ስህተት የለም፡፡

ነገር ግን በራስ መተማመን በራስ ገንዘብን እውን ከማድረግ ጋር መያያዝ አለበት፡፡ ምርት እያደገ፣ ኤክስፖርት እያደገ፣ ግብር እያደገ፣ ወዘተ ሲሄድ ነው የውስጥ አቅም ሊጨምር የሚችለው፡፡ በዚህ ዙሪያ ዕድገትና የአቅም መጎልበት ካልታየ ሊገኝ የታሰበው በጀት ላይገኝ ስለሚችል በዕቅዶች ላይ መጓተት ያስከትላል፡፡

የስኳር ፕሮጀክቶች በቂ በጀት እያገኙ አይደሉም፡፡ የምድር ባቡር ሥራው በበጀት በአስተማማኝ ደረጃ ላይ አይደለም፡፡ መንግሥት ከግል የኮንስትራክሽን ድርጅቶችና ከሌሎች ዓበይት ሥራዎችን ከሚሠሩ የግል ድርጅቶች ጋር ተዋውሎ ላሠራው ሥራ ለመክፈልም ሲቸገር እየታየ ነው፡፡ ሥራው ተሠርቷል ክፍያ ግን አልተፈጸመም፡፡  ሁሉም ችግር በገንዘብ  ባይመካኝም የገንዘብ እጥረት አንዱና ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡

ባንኮች ለደንበኞቻቸው በተገቢው ደረጃ ብድር እየሰጡ አይደሉም፡፡ ያላግባብ የሚሰጥ ብድርን ማረምና ማስተካከል ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን እየታየ ያለው ችግር ጉድለትን የማስተካከል ሳይሆን ለተገቢው ብድር ብቁና ንቁ ሆኖ አለመገኘት ነው፡፡

የውጭ ምንዛሪ ጉዳይም እንደዚሁ አስተማማኝ አይደለም፤ እጥረት አለበት፡፡ ሙስናም አለበት፡፡ የአቅም ማነስም አለበት፡፡ ውሸትም አለበት፡፡ ችግሩን በሀቅ፣ በግልጽና በድፍረት በመመርመር እንዴት እንፍታው ከማለት ይልቅ ‹‹በሽበሽ›› ነው እያሉ ማጭበርበር ይስተዋላል፡፡

መንግሥት ጠንካራ ቁጥጥር አደርጋለሁ ቢልም አሁንም ገንዘብ በሕገወጥ መንገድ ከአገር እየወጣ ነው፡፡ አሁንም ጥቁር ገበያው ተስፋፍቷል፡፡ እንዲያውም ከውጭ የሚመጣው የዳያስፖራ ኢትዮጵያውያን ገንዘብም የውጭ ምንዛሪ ክምችትን ከማሳደግ ይልቅ፣ በጥቁር ገበያ እየተመነዘረ ባንክ ሳይገባ እንዳለ ወደ ውጭ እየተጓዘ ነው ያለው፡፡ ከውጭ የመጣው ወደ ውጭ እየሄደ ነው፡፡ ኢትዮጵያ መተላለፊያ እንጂ መድረሻ መሆን አልቻለችም፡፡ የውጭ ምንዛሪ አሠራርን መንግሥት በፖሊሲ ደረጃ አስቸኳይ ትኩረት ሰጥቶ ዕርምጃ ሊወስድበት ይገባል፡፡ ጥቁር ገበያ እንዲጠፋ በይፋ ፈቃድ ለውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች እየሰጠ ባንክ ማስገባታቸውን ቢቆጣጠር ይበጃል፡፡ ለባንኮች ብቻ ኃላፊነትና ፈቃድ ሰጥቶ የውጭ ምንዛሪ ወደ ጥቁር ገበያ እንዳይገፋ መከላከል አለበት፡፡

ከውጭ የሚመጡ ዕቃዎችና ሸቀጦችም ዋጋቸው በእጅጉ እየናረ ነው፡፡ በብዛት ስለማይገኙ ዋጋቸውም የማይቻል እየሆነ ነው፡፡ ኤክስፖርት በማብዛት ኢምፖርት ለመቀነስ ቢታቀድም፣ ለኢምፖርት እየወጣ ያለው ገንዘብ ግን በእጅጉ ብዙ ነው፡፡ ከግሽበት ጋር በተያያዘ ምክንያት፡፡

በዚህ ምክንያትም ኅብረተሰቡ በኑሮ ውድነት በእጅጉ እየተጨፈለቀ ነው፡፡  ኑሮን ለመግፋት ደመወዝ ትርጉም የለሽ እየሆነ ነው፡፡ ስለቅንጦት ዕቃዎች አይደለም እየተነጋገርን ያለነው፡፡ ወይ ቅንጦት? ጤፉም፣ በቆሎውም፣ ልብሱም፣ ትራንስፖርቱም፣ ወዘተ በእጅጉ ውድ ሆነው ነው የሕዝቡን ኑሮ እያንገዳገዱ ያሉት፡፡ 

የገንዘብ ዝውውር ተዳክሟል፡፡ ገንዘብ የለኝም የሚል በዝቷል፡፡ ጨረታዎች እንደድሮው አይደሉም፡፡ ብዙ ተሳታፊዎችን አያገኙም፡፡ ሒሳቦች በወቅቱ እየተከፈሉና እየተዘጉ አይደሉም፡፡ በነገራችን ላይ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆኑ ባንኮች እንኳን ደንበኛ ካስቀመጠው ሒሳብ ለማውጣት ሲጠየቁ፣ እዚህ ቅርንጫፍ ገንዘብ ስለሌለ ከሌላ ቅርንጫፍ ውሰዱ ማለት ጀምረዋል፡፡ ያሳስባል፡፡ እንዴት ገንዘብ አይኖራቸውም?

ባንኮች ከሚያበድሩት 27 በመቶ ቦንድ እንዲገዙ የወጣው ፖሊሲም ባንኮች የሚያንቀሳቅሱትን ገንዘብ ውስን እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የባንኮች የገንዘብ እንቅስቃሴ ፈዘዝ እንዲል አድርጎታል፡፡ የዓለም ኢኮኖሚ እየተነጫነጨና እየተንገጫገጨ በመሆኑ የውስጥ ኢኮኖሚያችንን እንዲበረታታ አያደርገውም፡፡ ከውጭ ይገኝ የነበረውን ብድር ያስቀራል፡፡ ይገኝ የነበረውን ዕርዳታ ያጠፋል፡፡ ለጋሾችና አበዳሪዎችም ገንዘብ እያጡ ነውና፡፡ ይህም በቀላሉ የሚታይ ጫና አይደለም፡፡ ይቆነጥጣልና፡፡

በዚህ ላይ ሙስናና ብልሹ አስተዳደር አለ፡፡ ብዙ ዕቅድ ይዘናል ብዙ ገንዘብ ያስፈልገናል ብሎ ለአገርና ለሕዝብ ተቆርቁሮ ከመሥራት ይልቅ በዕቃ ግዥ ስም ለመስረቅ፣ በጨረታ ስም ጉቦ ለመቀበል፣ ሥራ ለማስፈጸም በእግር አትምጡ በእጅ እንጂ በማለት ባለው የገንዘብ ችግር ላይ ተጨማሪ የገንዘብ ችግር የሚፈጥሩ አሉ፡፡ ኢንቨስትመንትን የሚያዳክሙ፣ ኢንቨስተሮችን የሚያሸሹ፣ የአገር ሀብትን ለግል ጥቅም ለማዋል የሚሯሯጡ ሞልተዋል፡፡ ግፋ ቢል የሚታሙ እንጂ ጠንከር ያለ ዕርምጃ የማይወሰድባቸው አሉ፡፡ በየጊዜው እየበዙና እየተበራከቱ የመጡ፡፡

እነዚህና ሌሎች በርካታ ነገሮች ናቸው ኢኮኖሚውንና ቢዝነሱን እያፈዘዙ ያሉት፡፡ እናነቃቃው፡፡

ከሁሉም በፊት ሀቅን በድፍረት መቀበል ያስፈልጋል፡፡ የበጀት ችግር አለ ሲባል ኧረ የለም እያሉ መግለጫ መስጠት፣ የውጭ ምንዛሪ ችግር ሲባል ኧረ በሽ በሽ ነው እያሉ መደስኮር ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ትዝብት ነው ትርፉ ተብሎም መታለፍ የለበትም፡፡

በድፍረት ሀቅን እንወቅ፣ እንቀበል፣ ትክክለኛ መፍትሔ እንድናገኝ፡፡
መንግሥትና ኅብረተሰቡ ስለኢኮኖሚና ቢዝነስ የሚነጋገሩበት አገራዊ ‹‹የኢኮኖሚ ፎረም›› ያስፈልጋል፡፡ መንግሥት ብቻዬን አጥንቼና አስቤ ብቻዬን መፍትሔ እሰጣለሁ ማለት የለበትም፡፡ የኅብረተሰቡን አቅምም መጠቀም አለበት፡፡ የባለሙያዎችንና የባለድርሻ አካላትን ዕውቀትም ሊያገኝ ይገባዋል፡፡ ስለሆነም በፎረሙ እነሱንም ያሳትፍ፡፡

በጋራ መንቀሳቀስ ከተቻለ፣ ኅብረተሰቡና መንግሥት በሀቅና በግልጽ በአገር ችግር ላይ ከተወያዩና መፍትሔ ከፈለጉ መልስ ይገኛል፡፡ ችግር ይፈታል፡፡ አሁንም በአስቸኳይ መደረግ ያለበት ይኼው ነው፡፡
ኢኮኖሚውና ቢዘነሱ ፈዟል! እናነቃቃው!
  http://www.ethiopianreporter.com/index.php/editorial/item/1638-%E1%8A%A2%E1%8A%AE%E1%8A%96%E1%88%9A%E1%8B%8D%E1%8A%93-%E1%89%A2%E1%8B%9D%E1%8A%90%E1%88%B1-%E1%8D%88%E1%8B%9F%E1%88%8D-%E1%8A%A5%E1%8A%93%E1%8A%90%E1%89%83%E1%89%83%E1%8B%8D-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8C%82

Comments

  1. የሰማይ ሀብት ብድር ድርጅት እኛ ብድርን በወለድ መጠን 0f 3% እንሰጣለን ፡፡

    መልካም ቀን ጌታ / ማ am.

    እኛ የግል ኩባንያ ነን እናም የብድር መጠንን ለመወሰን በዝቅተኛ ወለድ ብድሮችን እናቀርባለን ለቢዝነስ ልማት በ 1000 ዩሮ ብድር ከ 100 ሚሊዮን ብድር ድንጋጌዎች መካከል የጠርዝ / የንግድ መስፋፋት ተወዳዳሪነት ፡፡

    (የዋትሳፕ ቁጥር +79652625435)

    የተለያዩ ብድሮችን እናቀርባለን

    * የግል ብድሮች (ደህንነቱ የተጠበቀ እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ)
    * የንግድ ሥራ ብድሮች (ደህንነቱ የተጠበቀ እና ደህንነቱ ያልተጠበቀ)
    * የማጠናከሪያ ብድር

    የቅድመ ክፍያ ክፍያዎች የሉም

    ይህንን ማስታወቂያ ለማንበብ ጊዜ ስለወሰዱ እናመሰግናለን ለበለጠ መረጃ እና ጥያቄዎች ዛሬ ለእኛ ኢሜል ይላኩልን

    skywealthloanfirm@gmail.com
    skywealthloanfirm@gmail.com
    skywealthloanfirm@gmail.com

    ወይዘሮ ሜሪ ሜሰን።

    ReplyDelete

Post a Comment

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር