የሀዋሳ ከተማን የቄራ አገልገሎት ለማሻሻል አዲስ ፕሮጀክት እየተካሄደ ነው

ሃዋሳ ሚያዚያ 10/2005 የሀዋሳ ከተማን የቄራ አገልግሎት ለማሻሻል በ25 ሚሊዮን ብር በጀት የተጀመረው አዲስ ፕሮጀክት ግንባታ በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ገለጸ፡፡ በማዘጋጃ ቤቱ የመሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መብራቴ መለሰ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በአለም ባንክ ፣ በክልሉ መንገስትና በከተማው ወጪ የሚካሄደው አዲሱ የቄራ አገልግሎት ፕሮጀክት ግንባታ የተጀመረው በ2003 መጨረሻ ላይ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ ግንባታ ከአጠቃላይ ስራው 75 በመቶ መጠናቁቅንና በዕቅዱ መሰረት ስራው እየተፋጠነ ይገኛል ብለዋል፡፡ ለስጋ ፍጆታ የሚውሉ በግና ፍየልን ጨምሮ በቀን ከ400 በላይ የእርድ እንስሳትን የማሰተናገድ አቅም ያለው አዲሱ የቄራ ፕሮጀክት ለሁለቱም ሀይማኖቶች የሚያገለግል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የቀድሞ ቄራ ከበሬ በቀር የፍየልና በግ እርድ ያልነበረው ፣ከከተማው ፈጣን ዕድገትና ከተጠቃሚው አንጻር የማስተናገድ አቅሙ በቂ ባለመሆኑ ይህንን ለማሻሻል አዲስ ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን ተናግረዋል፡፡ በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት መንግስት በሰጠው ትኩረት የሚካሄደው ፕሮጀክት ከነባሩ የተሻለና የጥራት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎቱን ለማቀላጠፍ ፣ የከተማውን ዕደገትና የተጠቃሚውን ፍላጎት የሚያሟላ ነው ብለዋል፡፡ የፕሮጀክቱ ግንባታ የህንጻና የኤሌክቶሮ ሜካኒካል ስራዎችን አካቶ በዘንደሮ አመት መጨረሻ ላይ መሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልገሎት ሲበቃ ጥራትንና ቅልጥፍናን ያሻሽላል፡፡ ህገወጥ እርድን በመቆጣጠር ከጤና ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን ለማስቀረት የሚያስችል ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የቀድሞ ቄራ እንዳለ ሆኖ አዲሱ ፕሮጀክት ራሱን ችሎ የሚያገለገል መሆኑም ተመልክቷል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=7126&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር