በለኩ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የሚሸጥ መድሃኒት እየተበራከተ ነው.......ነዋሪዎች

አዋሳ ሚያዚያ 15/2005 በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በሌኩ ከተማ በሀገ ወጥ መንገድ በከተማው የሚሸጡ መድሃኒቶች መበራከት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ በከተማው በገበያ ፣በመንገድ ዳርና ሱቆች በህገ ወጥ መንገድ የሚሸጡ መድሃኒቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መቷል፡፡ ይህም ለነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት እንደፈጠረባቸው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሪፖርተር አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ከነዋሪዎቹ መካከል ወይዜሮ ጥሩወርቅ ወልዴ፣ ወይዜሮ አበባው በቀለና ወይዘሮ ምትኬ ጫኒያለው እንዳሉት በተለይ ረቡዕና ቅዳሜ መድሃኒቱ ገበያ ላይ እንደማንኛውም ሸቀጥ ቀርቦ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ መድሃኒቱ የሚሸጠው ምንም ስለመድሃኒቱ ዕውቀት በሌላቸው ግለሰቦች መሆኑ ጉዳዩን እጅግ አሳሳቢ እድሮጎታል፡፡ በተለይ የሰው መድሃኒት ከከብቶች፣ ከበግና ከፍየል በድሃኒቶች ጋር አንድ ላይ ተቀላቅሎ መሸጡ የነገሩን አሳሳቢነት በህብረተሰቡ ዘንድ እንዲጨምር ማድረጉን ነዋሪዎቹ ገልፀዋል፡፡ የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ቡርሶ ቡላሾ ነዋሪዎች ያነሱት ቅሬታ ትክክል መሆኑን በማመን ችግሩን ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ከወረዳ አስተዳደር፣ ከፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት ለመስራት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ ህገ ወጥ መድሃኒቶቹ ጎረቤት ወረዳዎችና ዞኖች በማቋረጥ ወደ ከተማ የሚገቡ ስለሆነ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ከአጎራባች ወረዳዎችና ዞኖች ጋር በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎችን ከዳር ለማድረስ የህብረተሰቡ የተቀናጀ ትብብርና እገዛ ወሳኝ በመሆኑ በህገ ወጥ መንገድ በመድሃኒት ንግድ የተሰማሩ ግለሰቦችን በማጋለጥ ህብረተሰቡ እንዲተባበር ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=7329&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር