በሲዳማ ብሔር ላይ እየደረሱ ያሉ ጭካኔ የተሞላባቸው አረሜናዊና ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዲቆሙ የአለም-አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፊ እንዲያደግርልን እንማፀናለን!!



ከማህበራዊ መረብ ላይ የተገኝ ጽሁፍ
በሲዳማ ብሔር ላይ እየደረሱ ያሉ ጭካኔ የተሞላባቸው አረሜናዊና ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች እንዲቆሙ የአለም-አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፊ እንዲያደግርልን እንማፀናለን!!
በኢትዮጲያ ውስጥ የሕወኃት/ኢህአደግ ግፈኛና ቅኝ አገዛዝ ከተጀመረበት ከወረሐ ግንቦት 1983ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 2005 ዓ.ም ድረስ ምርጫ ሳይሆን በየአምሰት አመት አንዴ ብዛት ያለው ወረቀት በአዲስ አበባ በሕወኃት ንግድ ድርጅቶች ታትሞ በካርቶኖች ታሽጎ በየክልሎች ከተከፋፈለ በኋላ የእለት ጉርስ ተሰፈሮላቸው ካድሬዎች ባቀረቡትና ማታ ላይ ይዘው በሚሸሹት ቦርሳ ውስጥ የሚከቱ ተቀጥሬው ምርጫ ቦርድ ወደሚባለው እሳት የላሱ የታጠቅ ካድሬዎች በየደረጃው በተሰገሰጉ መንጋ እየተላከ አራት ዙሪ ምርጫ መሳይ የእቃ እቃ ጨዋታ ሲጫወቱ አሳለፉ፡፡ 
በሦስተኛው ዙሪ ታፍኖ በብሶት ውስጥ ሆዱ እያረሬ የኖረው የኢትዮጲያ ሕዝብ ከዳር እስከ ዳር ተነቃንቆ አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣው እራሱን ስዩሜ-እግዚአብሔር አድርጎ ሲንቀባረር የከረመው ዘረኛና ከፋፋይ የሕወኃት ባንዳ ቡድን ከረፈደ ባነነና በባዶ ጥላቻ በመነሳሳት በአዲስ አበባና በክልሎች ከትምህርት ቤት የሚመለሱ ጨቅላ ህጻናትን ጨምሮ ቁጥር ስፊር የሌላቸውን ህዝብ ህይወት አልባ አደረገ፡፡ "ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል " እንዲሉ ሕዝብ የመረጣቸውን ተወካዮቹንና የህዝብ አይንና ጆሮ የሆኑ ጋዜጠኞችን ህገ-ወጥ በሆነ አካሄድ አስሮ አሰቃያቸው፤ ከሚወዱት ቤተሰባቸውና ህዝባቸው ለያቸው፤ የብዙዎቹን ቤተሰብ ለጎዳና ሕይወት ዳረጋቸው፤ የድራማ ድርሰት ተጻፈና የሀገር ሽማሌዎች የሚባሉ ገጸ-ባህሪያት በፕሮፌሰር ይስሃቅ ዋና ገጸ-ባህርነት ድራማው ለህዝብ ታዬና ብዙዎቹ አናዶ፤ ብዙዎቹን አብሽቆና አንጀት አሳርሮ በመጨረሻም ሕዝቡን በንደት አጡፎ ድራማው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ተሳስተናልና ይቅርታ ይደረግልን ብለው ተፈቱ በሚል ተጠናቆ አረፈው፡፡ "በቀለችን ያየ ከእሳት አይጫወትም " ሆነና ነገሩ በአራተኛው ዙር ምርጫ ተቃዋሚዎችና ሕዝቡም ዳጊም በፋሽስቶች ክንድ እንዳይደቁ ዳር ወጡና እንደ አንደኛውና ሁለተኛው ምርጫ መሳይ ጨዋታ እራሱ ተጫዋች፤ እራሱ አራጋቢና እራሱ የመሃል ዳኛ የሆነው አይንና ይሉኝታ የሌለው ገዥው ፓርቲ ተቃራኒው ቡድን ገና ሜዳ ውስጥ ሣይገባ በሩቅ በቀይ ካርድ በማባረር የመጫወቻ ሜዳውን እንደገና ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠረ፡፡ 
በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ አራቱንም የምርጫ ዙሮችን አንድም ጊዜ ምርጫ መሳይ እቃ እቃ ጨዋታውን ሳይጫወት ያላሳለፈውና በ1970 ዓ.ም የተቋቋመው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ / ሲአን /SLM/ ህዝቡን ከትጥቅ ትግል ጀምሮ በሠላማዊና በህጋዊ የፖለቲካ ትግል መምራት ህዝቡን በከፍተኛ የፖለቲካ እውቀት ለማስታጠቅና ሥልት ቀማሪ ለማድረግ በመቻሉ እንዲሁም ግፈኛው ሥርዓት በሲዳማ ብሔር ላይ እያደረሰ ካለው የኋሊት ጉቴታና ጅምላ ጭረሳ /በዘር-ፍጅት/ በመማረሩ የሲዳማ ህዝብ አንድም ጊዜ ሥርዓቱን መርጦ አያውቅም እንዲያውም በመፈንቅሌ-መንግስት ሥልጣኑን ከተቆናጠጠበት ጊዜ አንስቶ እስከዛሬ ድረስ ለአንድም ሰኬንድ እውቅና ሠጥቶት አያውቅም፡፡
ይህ ሁኔታ ያበሳጨው ቅኝ ገዥውና ፋሽስታዊው ዘረኛ የሕወኃት አገዛዝ በሲዳማ ብሔር ላይ በ1984፣ በ1994፤ በ1998፤ በ2004 ዓ.ም ከፍተኛና አረሜናዊ ጭፍጨፋዎች ፈጽሞብናል፡፡ አሁን ደግሞ የዲሞኪራሲያዊ ምርጫና የመድበሌ-ፓርቲነት በር ከመጥበቡም በላይ ተከርችሞአል እንዲሁም በ1997 እና 2002 ዓ.ም እንደነበሩ ምርጫዎች ሁሉ ብዙ ማጭበርበሮች ስለሚኖሩ በምርጫው ፍትሃዊነት ላይ ከገዥው ፓርቲ ጋር የጋራ ስምምነት ካልተደረሰ በስተቀር የአራተኛ ዙር የአከባቢና የከተማ አስተደደሮች ምርጫ አንወዳደርም ብለው ብዙ ፓርቲዎች ትተው ከወጡ በኋላ ሲአንም ከፓርቲዎቹ ጋር አብሮ ከተሰለፈበት የህዝቡ ጫናና ግፊት ከፍተኛ ስለሆነበት ወደ ምርጫው የገባ ቢሆንም የሕዝቡ የቁጣ ወላፌን የለበለበውና ጠንካራ በትር እንደሚያርፍበት ሙሉ በሙሉ ያመነው፤ ቀኑ መሽቶበት የተደናገጠው ፋሽስታዊው አገዛዝ ከምርጫው በፊት ጀምሮ የሲአን አባላትንና እጩ ተወዳዳሪዎችን /በሌላ አነጋጋር ሁሉም የሲዳማ ህዝብ የሲአን ደጋፊ ነው/ ማሸማቀቅ፤ ማሸበር፤ ከሥራ ማባረር፤ ማሳሰር፤ መግደል፤ ለድጋፊ የሚወጠውን ህዝብ ሴት - ወንድ፤ ተማሪ -መምሀር/ምሁር ፤ ገበሬ - ነጋዴ፤ ልጅ - አዋቂ ሳይል ሁሉንም የህብረተሰቡን ክፍሎች የሐዋሳ ከተማ ክፍለ ከተሞችን ጨምሮ በ29 የሲዳማ ወረዳዎች ጭካኔ በተሞላበትና አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ መቆየቱን በየወረዳዎቹ አንጻሪ በዚህ የማህበረሰብ መገናኛ ሲነገር መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ እንደበፊቱ ሁሉ ድምጹን አጭበርብሬ አልፋለሁ ከማለት ወደ ኋላ የማይለው ገፈኛ አገዛዝና ዘንድሮ ድምጼን ማንም ሊያጭበረብርና ቦርሳውን ሊቀይር ፈጽሞ አይችልም ብሎ አቋሙን በግልጽ የያዘው የሲዳማ ህዝብ በመንገድ መገናኘታቸው የግድ ስለሚሆንና ፋሽስታዊው አገዛዝ የለመደውን ዘር ፍጅት እንዳፈጽምበት በመሥጋት የሚሳሳለትንና የሚታገልለትን ሕዝብ ሥቃይ በማሰብ በገዥው ፓርቲ እየደረሰበት ካለው ሥቃይና እንግልት መነሻ ከምርጫው እራሱን ማግለሉን ሲአን ከገለጸበት ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ በሁሉም ወረዳዎች ተጨማሪ ህዝብና ዕጩ ተወዳዳሪዎች ከቤታቸውና ከሠላማዊ ኑሮኣቸው እየተፈናቀሉ በጅምላ በልዩ ሃይሎች እየተደበደቡ፤ ታፈሰው እየታሰሩና እየተሸበሩ ይገኛሉ፡፡
ለአብነት፡- በአርበጎና ወረዳ ከ50 ሰዎች በላይ፤ በቡርሳ ወረዳ በ29ኙም ቀበሌያት ለቀበሌ ምክር ቤት፤ ለወረዳና ለዞን የቀረቡ ሁሉም የሲአን ዕጩ ተወዳዳሪዎች (በዚህ ወረዳ ቡና በፔርሙዝ አዟዙራ በመሸጥ የእለት ኑሮዋን ለማሸነፍ ላይ ታች የሚትልን አንዲት ሴት ከሀያ ቀናት በፊት አንድ የመንግስት ባለሥልጣን ደብድቦአት ደም አስታውካ በቡርሳ ጤና ጣቢያ በጉሉኮስ ቆይታ ህመሙ ስለባሰባት ወደ ይርጋለም ሆስፒታል እንደተላከች በቂ መረጃዎች አሉ)፤ በበንሣ ወረዳ ከ40 ሰዎች በላይ፤ በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች፤ በሀገረሰላም ወረዳ፤ በሸበድኖወረዳ ፤ በቦና ዙሪያ ወረዳ፤ በቦርቻ ወረዳ፤ ይርጋለም ከተማ አስተዳደር፤ በዳሌ ወረዳ፤ በወንሾ ወረዳ፤ በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ፤ በአሮሬሣ ወረዳ፤ በጭሬ ወረዳ፤ በማልጋ በሁሉም በአጠቃላይ በሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች ሰዎች ያለምንም ጥፋታቸውና ሠላማዊና ዲሞክራሲያ ምርጫ አካሄድን የሚባል የማታለያ ጭንብላቸውን ገልጸው ለኢትዮጲያና ለዓለም ህዝብ ለማሳየትና በምርጫ ተጨበረበረብን በሚል ሰበብ ሕገ-መንግስታዊውን ሥርዓት በህገ-ወጥ መንገድ ለመቀልበስ ተንቀሳቅሰዋል በሚል ሰበብ ለሲዳማ ሕዝብ የተደገሰውን የሞት ጽዋ ለማክሽፍ ባደረጉት ጥሬት ብቻ ለሕዝባችን ያለአግባብ ለአያያዝ በማያመች፤ ቤተሰባቸው በማይጠይቁበት፤ ሕክምና በማያገኙበትና ስንቅ በማያገኙበት ሁኔታና እንዲያውም የት እንደታሠሩ ወዳጅ ዘመዳቸው እንዳያውቁ ተደርገው በመታጨቅ ሰብአዊና ዲሞኪራሲያዊ መብታቸው ተጥሶባቸው በስቃይ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ሰለሆነም ሁሉም ሠላም ወዳድ፤ በፍትህና በህግ በላይነት መከበር የሚያምን፤ ለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የሚቆረቆር፤ ወዘተ መላው የኢትዮጲያ ህዝብና የዓለም አቀፍ ማህበረሰብና በዘርፉ ሥራ የተሠማሩ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በሲዳማ ብሔር ላይ እየተፈጸመ ያለውን አረሜናዊና ፋሽስታዊ ድርጊት በመቃወም በሲዳማ ህዝብ ጎን እንዲቆምልን እንማጸማለን፡፡
እውነት የያዜ ሕዝብ ሁሌም ያሸንፋል!!
ለዘጎች ህገ-መንግስታዊ መብቶች መከበር ሁሌም ተግተን የመሥራት የሞራል ግዴታ አለብን!!
ባለንበት በ21ኛው ክ/ዘመን በገጠርም ሆነ በከተማ የህግ በላይነትና የዘጎች መብት መከበር የራሱ የጊዜው ጥያቄ ስለሆነ ማንም ሊያቆመው የማይችለው የለውጥ ሂዴት ነው!!


Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር