ሲዳማ ዞን ውስጥ መዋለ ንዋይ የሚያፈሱ ባላሃብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሽቆልቆል ላይ ነው፤ ባለፈው በጀት ኣመት በዞኑ ከ 267 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘጋቡ ባላሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ ሲሆን በዚህ ኣመት ግን 15 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ያስመዘጋቡ ባላሃብቶች ብቻ ናቸው ፍቃድ የወስዱት

አዋሳ ሚያዚያ 09/2005 በሲዳማ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት 15 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ፈቃዱ የተሰጠው በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ለመሰማራት ጥያቄ ላቀረቡ አምስት ባለሃብቶች ነው፡፡ ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ ግብርናና ኢንዱስትሪ እንደሚገኙበት አስታውቀዋል፡፡ ባለሃብቶቹ በሚያካሂዱዋቸው ኘሮጀክቶች ለ100 ቋሚና 994 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡ መምሪያው በገጠር የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጥናትና በመለየት ለባለሃብቶች ከማስተዋወቅ በተጨማሪ በግብርና፣ በማህበራዊ አገልግሎትና በኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብተቶች ከ620 ሄክታር በላይ የገጠር መሬት መስጠቱን የስራ ሂደቱ አስተባባሪ ተናግረዋል፡፡ ከባለሃብቶች መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት ልማታዊ መንግስት ለግል ኢንቨስትመንት እያደረገ ያለው ድጋፍና እገዛ በርካታ ባለሃብቶች በሀገር ውስጥ እንዲፈጠሩ ከማድረጉም ባሻገር በድህነት ላይ ለሚደረገው ትግል የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉና ለብዙዎች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ከፍተኛ እገዛ እያደረገ በመሆኑ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ በሲዳማ ዞን ባለፈው በጀት ዓመት ከ267 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 45 ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የተሰማሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=7107&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር