በሴቶች ጥሎ ማለፍ ሲዳማ ቡና ለግማሽ ፍፃሜ አለፈ


በኢትዮጵያ ሴቶች ጥሎ ማለፍ ሲዳማ ቡና መብራት ሃይልን በመል ጨዋታ በማሸነፍ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላል፡፡


መጋቢት5/2005 ይርጋለም ላይ በዝናባማው የአየር ሁኔታ ሲዳማ ቡና እና መብራት ሃይል ጨዋታቸውን አካሂደዋል፡፡በጨዋታው ሲዳማ ቡና 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

በመጀመሪያ ጨዋታቸው መብራት ሃይል 1 ለ 0 ያሸነፈ ቢሆንም በደርሶ መልስ ሲዳማ ቡና 2 ለ1 በሆነ አጠቃላይ ውጤት ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፍ ችሏል፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ከነማን ፣ደደቢት መከላከያን ፣ኢትዮጵያ መድህን ደግሞ ድሬዳዋ ከነማን በማሸነፍ ያለፉ ክለቦች ናቸው፡፡

በግማሽ ፍፃሜው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድህን ደደቢት ከሲዳማ ቡና ይገናኛሉ፡፡

ጨዋታዎቹ በሚቀጥለው ሃሙስ መጋቢት 13/2005 እንደሚካሄዱም ከወጣው መርሃ ግብር ማወቅ ተችሏል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር