ደኢህዴን ያስገነባው አዳራሽና ማሰልጠኛ ማዕከል ተመረቀ

አዋሳ መጋቢት 09/2005 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ከ64 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት ያስገነባው ቢሮ ማስልጠኛ ማዕከልና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ ተመረቀ። ድርጅቱ ከአባላት መዋጮ ባሰባሰበው ገቢ የክልሉን ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህላዊና ፖለቲካዊ እሴቶችን በሚያንጸባርቅ ሁኔታ ያስገነባውን ቢሮ ማሰልጠኛ ማዕከልና የመሰበሰቢያ አዳራሽ መርቀው የከፈቱት የደኢህዴንና ኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ናቸው። በ548 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባውና ለቢሮ አገልግሎት የሚውለው ባለሁለት ፎቅ ህንጻ 57 ለተለያየ አገልግሎት የሚውሉ ክፍሎችና አራት የመሰብሰቢያ አዳራሾችን የያዘ ነው። የጉባኤ አዳራሹ በአንድ ሺህ 790 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈና በአንድ ጊዜ አንድ ሺህ 360 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው ቁሳቁስ የተሟሉለትና ሶስት መለስተኛ የመወያያ ክፍሎች ፣የእንግዳ ማረፊያዎች ያሉት መሆኑ ተገልጿል። በአንድ ጊዜ ሁለት ሺህ 500 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ማስተናገድ የሚችለው የስልጠና ማዕከል 30 የስልጠና ክፍሎች ፣10 የአስተዳደር ቢሮዎችና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን የያዘ በአንድ ሺህ 760 ካሬ ሜትር ቦታላይ ያረፈ መሆኑ ተገልጿል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=6432&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር