በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሃዋሳ ከነማ ወደ መሪነት ተመለሰ


አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ሃዋሳ ከነማ እና መብራት ሃይል ድል ቀንቷቸዋል።
ሃዋሳ ከነማ ከቀኑ 9 ሰአት ከአዳማ ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ መሪነት ተመልሷል።
እዚህ አዲስ አበባ ላይ በተደረጉ ሁለት ጨዋታወች ደግሞ እስካሁን ማሸነፍ ያልቻለው ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ፥ በኢትዮጵያ መድን 2 ለ 1 ተሸንፏል።
11 ሰአት ላይ በተደረገ ሁለተኛ ጨዋታ መብራት ሃይል ሙገር ሲሚንቶን 3 ለ 0 በማሸነፍ ፥ ደረጃውን ወደ አራተኛ አሻሽሏል።
ፕሪሚየር ሊጉን ሃዋሳ ከነማ በ22 ነጥብ ሲመራ ፥ ደደቢት በ21 እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ19 ነጥቦች ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።
ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ደግሞ ከ10 ጨዋታዎች ባገኘው አንድ ነጥብ የደረጃውን ግርጌ ይዞ ይገኛል።
የፕሪሚየር ሊጉ 11ኛ ሳምንት በመጭው ረቡዕ እና ሃሙስ ተካሂዶ ፥ በብሄራዊ ቡድኑ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ምክንያት ለ3 ሳምንታት ይቋረጣል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር