ደኢህዴን በአለታ ወንዶ ወረዳ ከ5ሺ800 በላይ ዕጩዎችን ለዉድድር አቀረበ

ሃዋሳ መጋቢት 6/2005 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የከተሞችና የአካባቢ ምርጫ በአለታ ወንዶ ወረዳ ከ5ሺህ 800 በላይ ዕጩዎችን ለዉድድር ማቅረቡን አስታወቀ ። በወረዳው የንቅናቄዉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሀላፊ አቶ ከበደ ቱሚቻ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በምርጫው ንቅናቄውን ወክለው ለመወዳደር ከተዘጋጁት መካከል ግማሽ ያህሉ ሴቶች ናቸዉ ። ንቅናቄዉ እጩ ተወዳደሪዎችን ለምርጫ ያቀረበዉ በህዝብ ካስገመገምና ብቁነታቸዉን በይሁንታ ካረጋገጠ በኋላ መሆኑን አስታዉቀዋል ። ድርጅቱ ካዘጋጃቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎች መካከል አምስቱ ለዞን ምክር ቤት፣ 87 ለወረዳ ምክር ቤቶች ቀሪዎቹ ደግሞ ለቀበሌ ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ መሆናቸዉን ገልጠዋል ። ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ ግልጽና በህዝብ ዘንድ አመኔታ አግኝቶ እንዲጠናቀቅ በንቅናቄው ደረጃ ሰፊ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን አቶ ከበደ ጠቁመው በቀጣይነትም ሀዝቡ በመብቱ ተጠቅሞ የመሰለውንና ይበጀኛል የሚለዉን እንዲመርጥ አሳስበዋል ። ንቅናቄዉ ከተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር የጋራ ምክር ቤት አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን አመልከተው እስካሁን በምርጫው ለመሳተፍ የሚንቀሳቀስው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ ቢሆንም በምርጫው ከማይሳተፈው ከኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ ጭምር በጋራ ምክር ቤቱ አብረዉ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልጠዋል ። በሌላ በኩል ደግሞ በወረዳው ለሚካሄደው ለዚሁ ምርጫ 58ሺህ 854 ህዝብ ተመዝግቦ ለመራጭነት የሚበቃውን ካርድ መውሰዱን የወረዳው ምርጫ ጽህፈት ቤት አስተባበሪ አቶ ወርቁ አኔቦ አመልከተዋል፡፡ ለመራጭነት ከተመዘገበው ህዝብ ውስጥ ከ27 ሺህ የሚበልጡት ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመው በዕጩ ተወዳደሪነትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ህዘቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ/ደኢህዴን/ ሌላ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ/ሲአን/ ለዞን ምክር ቤት አምስትና ለወረዳ ምክር ቤት ደግሞ 86 ዕጩዎችን ማስመዝገቡና በቀበሌ ደረጃ ግን እንዳልተሳተፉ አስረድተዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር