ከተፈሪ ኬላ ሀገረሰላም ጋታሜ ቦናን ጨምሮ በደቡብ ክልል ሶስት ዞኖች ከ42 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የመንገድ ግንባታ እየተካሄደ ነ

 ዲላ መጋቢት 08/2005 በክልሉ ሶስት ዞኖች ከ42 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የአዳዲስና ነባር መንገዶች ግንባታ በማከናወን ላይ መሆኑን የደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣን የዲላ ዲስትሪክት ገለጸ። የትራንስፎርሜሽን እቅዱን በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረገ በመንገድ ዘርፍ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ ጉልህ ድርሻ እንዳለው የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ገለጹ። በደቡብ ክልል መንገዶች ባለስልጣን የዲላ ዲስትሪክት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዩሃንስ ዱከሌ ትናነት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከያዝነው ዓመት ጀምሮ በጌዴኦ ሲዳማና ሰገን ህዝቦች ዞኖች 200 ኪሎሜትር አዲስና ከ500 ኪሎ ሜትር በላይ ከባድና ቀላል የመንገድ ጥገና ስራ እያከናወነ ይገኛል። ለመንገዱ ጥገና መንግስት 22 ሚሊዮን ብር ለአዲስ መንገድ ስራ ከ19 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን ገልጸው መንገዶቹ ወረዳዎችን ከዞን ከተሞችና ዞኖችን ከዞን የሚያገናኙ ደረጃቸውን በጠበቀ ሁኔታ የሚገነቡ መሆኑ አስታውቀዋል። አዲስ ከሚገነቡት መንገዶች መካከል በጌዴኦ ዞን ከገደብ ወርቃ ጎቲቲ 60 ኪሎ ሜትር ፣በሰገን ህዝቦች ዞን ከሶያማ ሰገን ከተማ ፣በሲዳማ ዞን ከተፈሪ ኬላ ሀገረሰላም ጋታሜ ቦና እንደሚገኝበት ገልጸዋል። የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበባየሁ ታደሰ በበኩላቸው መንግስት የትራንስፎርሜሽን እቅዱን ተግባራዊ ለማድረገ ከዘረጋቸው የልማት ስራዎች መካከል ዋነኛው መንገድ መሆኑን ተናግረዋል። ባለፈው አመት በተጀመረው የቀበሌ ተደራሽ መንገድ ከ116 ኪሎ ሜትር የሚበልጥ መንገድ መጠናቀቁን ገልጸው በመንግስት በጀት የተያዘላቸው የገደብና ይርጋጨፌ ኢዲዶ መንገድ ፕሮጀክቶች በክልሉ መንገዶች ባለስልጣን እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። አርሶ አደሩ በተለይ የቡና ምርቱን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለእንዱስትሪዎች በማቅረብ ምርቱ በወቅቱ ለማእከላዊ ገበያ አንዲቀር ከማገዙም ሌላ የትምህርትና የጤና ቁሳቁሶችን በአጭር ጊዜ በማድረስ ለእቅዱ ስኬት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀዋል። በይርጋጨፌ ወረዳ የኢዲዶ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ክፍሌ ቃንቴና በገደብ ወረዳ ሀሎ በሬ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ቦጋለ በዴቻ በበኩላቸው የመንገዱ መሰራት ከዚህ በፊት ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት ከማሰቀረቱም ሌላ ምርታቸውን በቀላሉ ለገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር