በሃዋሳ ከተማ ከቱሪስቶች ከ39 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ገቢ ተገኘ

አዋሳ የካቲት 30/06/2005 በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ስድስት ወራት የቱሪስት መስብህ ስፍራዎችን ከጎበኙ የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች ከ39 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የአስተዳደሩ ባህል፣ ቱሪዝምና መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ ወይዘሮ ምህረት ገነነ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ገቢው የተገኘው በከተማው የሚገኙ ባህላዊ፣ የተፈጥሮና ታሪካዊ የመስብህ ሰፍራዎችን ከጎበኙ 103 ሺህ 408 እንግዶች ነው። የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ከሰባት ሚሊዮን ብር ብልጫ እንዳለው ጠቁመው ከቱሪስቶቹ መካከል 20ሺህ 612 የውጪ አገር ቱሪስቶች ናቸው ብለዋል፡፡ የቱሪስት ፊሰቱና ከቱሪዝም ዘርፍ የተገኘው ገቢ የጨመረው በሀገር ውስጥና በውጭ የከተማውን መልካም ገፅታ የሚያሳዩ የባህል ፌስተቫሎችና ልውውጦች ፣የማስታወቅያና ፕሮሞሽን ስራ በመሰራቱ እንዲሁም የቱሪስት አገልግሎት ተቋማትን ለማጠናከር በርካታ ስራ በመሰራቱ ነው ብለዋል፡፡ የቱሪዝም መረጃዎችን በመጠቀም የማስተዋወቅ፣ ለአስጎብኝዎች ስልጠና መስጠት፣ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በጥናት ተለይቶ ለጎብኝዎች ክፍት ማድረግና የከተማውን የቱሪዝም አቅም የተሟላ መረጃ መስጠት የሚችል "ቱሪዝም ፖቴንሻል ኦፍ ሃዋሳ ሲቲ" በሚል የተዘጋጀ መፅሔት በመሰራጨቱ ገቢው ለጨምር መቻሉን ተናግረዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር