ሲዳማ ኔትን ጨምሮ 16 የኣሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት እገዳ ተጣለባቸው


አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ 16  የአሸከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ እገዳ ጣለ።

በደቡብ ክልል ፍቃድ አግኝተው ስልጠና የሚያካሂዱ 36 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትን ፥ በክልሉ የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ሲባል የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ  ተቋማቱን  በአመታዊ እቅዱ ያሳትፋቸዋል።
የቢሮው ሃላፊ አቶ ታገሰ ኤሮሞ እንደሚሉት ፥ እንዲሳተፉ በተደረገበት እቅድ ደግሞ አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም ለማሰልጠን ሊያሟላ የሚገባቸው መስፈርቶች ተካተዋል።
የክልሉ ትራንስፖርት ቢሮ ባለሙያዎች በተቋማቱ ላይ ባደረጉት ግምገማ ፥ 8 ያህሉ በተገኘባቸው ጉድለት በማስጠንቀቂያ ሲታለፉ ፥ 16ቱ ደግሞ ስልጠናውን  የሚሰጡበት ተገቢ ቦታ  የሌላቸው ፣ የራሳቸው የማለማመጃ  መኪና ሳይኖራቸው በኪራይ የሚጠቀሙ  ፤ በቂ ክህሎት ያለው አሰልጣኝ ሳይኖራቸው በመስራታቸው እርምጃው ሊወሰድባቸው እንደተቻለ ይናገራሉ።
12 ተቋማት ደግሞ በተካደው ግምገማ አንጻራዊ ለውጥ በማምጣታቸው ያለምንም ማስጠንቀቂያ ስራቸውን እንዲቀጥሉ የተደረጉ ናቸው።
በቤንች ማጂ ፣ ስልጤ ዞን ወራቤ ፣ ጋሞ ጎፋ ፣ ሲዳማ ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጉራጌ ዞኖች ላይ የሚገኙ  ናቸው እነዚህ ተቋማት።
ሲዳማኔት ፣ ፊውቸር ላይት ፣ ዎስመካ  ፣ ጋላክሲ ፣ መካነ ኢየሱስ ፣ መገናኛ ፣ ወራቤኬሪ ፣ ፍሬም ፣ ኢሻ ፣ ዱዛ ፣ ጂፎር ፣ ወገሹር ፣ አግነት ፣ እና ሚቴማ እርምጃው የተወሰደባቸው ተቋማት ናቸው።
ተቋማቱ በስልጠና ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን በተጓደለ መልኩ እንዳያስመርቁም  ፤ በየጊዜው ልዩ ክትትል እየተደረገባቸው ስልጠናውን እንዲጨርሱ  አቅጣጫ መቀመጡን ነው ሃላፊው የተናገሩት።
እገዳ ስለተጣለባቸው ተቋማት ህብረተሰቡ እንዲያውቅና  በአዳዲስ የአሽከርካሪ ተቋማት ለመሰልጠን ሲፈልጉ ፥ ወደ ተሻሉ ተቋማት እንዲያመሩ የሚያመላክት ጽሁፍ በየስፍራው  ተቀምጧል።
ለ 3 ወራት አዳዲስ ሰልጣኞችን እንዳይቀበሉ ይታገዱ እንጂ ፥ ጽህፈት ቤታቸውን በአሰራሩ መሰረት አጣነክረው  ወደ ለውጥ ከገቡ  እገዳው ሊነሳላቸው ይገባል ነው ያሉት።
 ምንጭ ፋና ሬድዮ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር