ከሲዳማ ዞን ባለፉት ሰባት ወራት ከ146 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

ሃዋሳ መጋቢት 2/2005 በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ባለፉት ሰባት ወራት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 146 ሚሊዮን በላይ ገቢ ሰበሰበሰ፡፡ ከ13 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ገቢ መሰብሰቡን የዞኑ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የዞኑ ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ እንደገለጹት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ገቢውን የሰበሰበሰው ከቀጥታ ታክስ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶቸ ከማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶች፣ከተጨማሪ እሴት ታክስና ታክስ ካልሆነ ገቢዎች ነው፡፡ ባለፉት ሰባት ወራት የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ13 ሚሊዮን በላይ ብር ብልጫ እንዳለውም አመልክተዋል፡፡ ገቢው ሊጨምር የቻለው ጽህፈት ቤቱ ለግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠናዎች መስጠት በመቻሉ፣ዘመናዊ የታክስና ቀረጥ መረጃ ስርዓት በመዘርጋቱና ተደራሽ ማድረግ በመቻሉ ነው ብለዋል፡፡ ባለፉት ሰባት ወራት 217 አዲስ ግብር ከፋዮች ወደ ግብር ስርዓቱ የገቡ ሲሆን ከነዚህ መካከል 19 የሚሆኑት ''ሀ'' ግብር ከፋዮች እንደሆኑ ጠቁመዋል። ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በይርጋለምና አለታወንዶ ከተሞች የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ለማስጀመር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጸው በበጀት ዓመቱ ከ344 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰበ አቅዶ ወደ ተግባር መግባቱን አቶ ተሻለ አሰታውቀዋል።
source: http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=6247

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር