በሲዳማ ዞን የማጅራት ገትር ወረርሽን ተከስቷል


አዲሰ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የተከሰተውን የማጅራት ገትር በሽታ በቁጥጥር ስር ለማዋል የተጠናከረ ጥረት እየተደረገ ነው ።
በአስር አመት አንድ ጊዜ የሚከሰተው የማጅራት ገትር (ማኔንጃይትስ) ወረርሽኝ ፥ ሰሞኑን በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ተከስቶ እንደነበር ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።
ከእነዚህም ውስጥ በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ፣ በጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማና አላባ አካባቢ ፥ ከ100 በላይ ምልክቶቹ የታየባቸው ሰዎች በላቦራቶሪ ምርመራ በበሽታው መያዛቸውን ማረጋገጥ ተችሏል ነው ያለው የክልሉ ጤና ቢሮ።
በሽታው ከመከሰቱ በፊት ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፥ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም የማስተማር ስራ መሰራቱን በጤና ቢሮው የህዝብ ግንኙነትና የጤና ኮሚዩኒኬሽን የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ቀድርላ አህመድ ተናግረዋል።
በሽታው ተከስቶባቸዋል ተብሎ የተረጋገጡ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው የመከላከል ስራ እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰው ፥ በሽታውን ለመቆጣጠር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው ብለዋል።
ወረርሽኙ ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች እንዳይዛመት  የበሽታው መመርመሪያ ማሽን በክልሉ በስፋት ተሰራጭቶ ስራዎች እየተሰሩ ነው ያሉት።
በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች በስጋት ያልተጣራ መድሃኒት እየወሰዱ በመሆናቸው ፥ በዚህ ዙሪያም አስፈላጊ ጥንቃቄ ህብረተሰቡ እንዲያደርግ ነው የጠየቁት።
ማህበረሰቡ ወደ ሌሎች አካባቢዎችም ይዛመታል ከሚል ከስጋት ነጻ ይሆን ዘንድም በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ መድሃኒቶች በስፋት እየተሰራጩ እንደሆነም ይናገራሉ።
ከቅድመ መከላከል ባለፈም በአርባምንጭ ከተማ ብቻ በበሽታው ተይዘው የነበሩ 53 ሰዎች ፥ ተገቢውን ህክምና የገኙ ሲሆን ፥ በሸበዲኖና አላባ አካባቢም መሰል ህክምና እና አገልግሎቶች እየተሰጡ ነው።
የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበኩሉ የመስክ ጥናት እንዲያካሂዱ ወደ ቦታው የአጥኚዎች ቡድን የላከ ሲሆን ፥ በአጠቃላይ በሽታውን በሚመለከት እየተደረገ ስላለው ስራም በቀጣይ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥበት ነው ያስታወቀው።http://www.fanabroadcasting.com/index.php?option=com_content&view=article&id=2251:2013-02-06-07-11-24&catid=102:slide

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር